Loading
Singer
ልቤም ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ይኅው ፡ አፈለቀ ውስጤን ፡ አረስርሶ ፡ በዛ ፡ አጥለቀለቀ መሬትን ፡ ፈንቅሎ ፡ ውኃ ፡ እንደሚወጣ ከልቤ ፡ የደስታ ፡ ጩኅት ፡ ዕልልታ ፡ ካፌ ፡ ወጣ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ /፫ ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው ያ ፡ አስቸጋሪው ፡ ዝናብ ፡ ክረምቱ ፡ አለፈ ድምጼን ፡ ላሰማ ፡ ተነሳው ፡ የዜማ ፡ ጊዜ ፡ ደረሠ ከአለት ፡ ንቃቃትና ፡ ከገደል ፡ መሰሰጊያው ፡ ማልጄ ፡ ልነሣ ፡ ልውጣ ፡ ከበሮዬን ፡ ላንሣው ፡ ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በመለከት ፡ እናመስግነው በበገና ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በመለከት ፡ እናመስግነው በበገና ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ /፫ ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ውስጤን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ባፌ ፡ ሚወጣው በግብጽ ፡ ምድር ፡ ውስጥ ፡ በኩር ፡ ሲመታ ፡ በሞት አንዱ ፡ ሌላውን ፡ እንዳይረዳ ፡ እርሱም ፡ ጋር ፡ ደረሰበት ምድሪቱም ፡ ስትናወጥ ፡ በለቅሶ ፡ በዋይታ ፡ ደሙ ፡ ከለላዬ ፡ ሆኖ ፡ አሰማለሁኝ ፡ ዕልልታ ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው ልቤም ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ይኅው ፡ አፈለቀ ውስጤን ፡ አረስርሶ ፡ በዛ ፡ አጥለቀለቀ መሬትን ፡ ፈንቅሎ ፡ ውኃ ፡ እንደሚወጣ ከልቤ ፡ የደስታ ፡ ጩኅት ፡ ዕልልታ ፡ ካፌ ፡ ወጣ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ ዕልልታ ፡ /፫ ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው ምድር ፡ ሁሉ ፡ እናመስግነው ፡ በክበሮ ፡ እናመስግነው በጸናጽል ፡ እናመስግነው ፡ በዕልልታ ፡ እናመስግነው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ቤቴን ፡ የሞላው ዕልልታ ፡ ነው ፡ ሠፈሬ ፡ ሚሰማው