Loading
Singer
ዕልል ፡ እልል ፡ ብዬ (፪x) ላከብርህ ፡ ነው ፡ ተራዬ (፪x) ፈርዖንም ፡ ቢፎክር ፡ የመረጥከውን ፡ ሊያስገብር ብዙ ፡ ጣረ ፡ ደከመ ፡ የአንተን ፡ ሀሳብ ፡ ሊቀይር ትእዛዝ ፡ ወጥቶአል ፡ ከሰማይ ፡ አታቆመው ፡ በአንተ ፡ ኃይል ላትነሳ ፡ ወድቀሃል ፡ ህዝቡን ፡ ፈቶኣል ፡ አዶናይ የተገለጠውን ፡ ብርሃን ሕይወት ፡ ሆኖ ፡ አየሁት ፡ በዓይኔ መኖር ፡ መርጫለሁ ፡ ዛሬ አቻ ፡ አልተገኘለት ፡ ክብሬ ኦሆ ፡ ክብሬ (፪x) አትሻር ፡ አትለወጥ ፡ የጸና ፡ ነው ፡ ዙፋንህ አታረጅ ፡ አትደክም ፡ ትኖራለህ ፡ በክብር ከስም ፡ በላይ ፡ ስም ፡ አለህ ፡ ከአብ ፡ ዘንድ ፡ የተሰጠህ ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ይንበርከክ ፡ ከፍ ፡ ላለው ፡ ይስገድ ዕልል ፡ እልል ፡ ብዬ (፪x) ላከብርህ ፡ ነው ፡ ተራዬ (፪x) በኃይል ፡ አይደል ፡ በብርታት መች ፡ በራስ ፡ ነው ፡ በጥረት በነጻ ፡ ነው ፡ ቸርነት በእርሱ ፡ ሆነ ፡ በመንፈስ (፪x) የተገለጠውን ፡ ብርሃን ሕይወት ፡ ሆኖ ፡ አየሁት ፡ በዓይኔ