Loading
Singer
የሞትንስ ፡ ፍርድ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ሰምተናል በሕይወት ፡ ለመኖር ፡ ዕለት ፡ ዕለት ፡ ሞተናል የኢየሱስን ፡ ሞት ፡ ተሸክመን ፡ ዞረናል በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ግን ፡ በምህረቱ ፡ ኖረናል አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ውኃ ፡ አስጥሞን ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን በእምነት ፡ እንጂ ፡ በምናየው ፡ አይደለም ከጌታ ፡ በቀር ፡ እኛ ፡ ትምክህት ፡ የለንም ጽድቃችን ፡ እንኳን ፡ ለዚህ ፡ አላበቃንም ፀጋው ፡ አጽንቶን ፡ ከርሱ ፡ አልተለየንም አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ውኃ ፡ አስጥሞን ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን ሕያዋን ፡ ሆነን ፡ በእርሱ ፡ እንኖራለን የጌታን ፡ ሥራ ፡ ዛሬም ፡ እንገልጻለን ክብር ፡ ለሥሙ ፡ ሞገስ ፡ ለሥሙ ፡ ብለን ያለንን ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ እንሰዋለን አዝ፦ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ጌታ ፡ ባይረዳን ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ሆኖ በችግራችን ፡ ባይታደገን ፡ እንደዚህ ፡ ፈጥኖ ረግረጉ ፡ ውጦን ፡ ልንጠፋ ፡ ነበር ፡ ውኃ ፡ አስጥሞን ዛሬ ፡ ግን ፡ ድነን ፡ በሕይወት ፡ አለን ፡ ኢየሱስ ፡ አውጥቶን