Loading
Singer
ቀን ፡ ተቀጥሮ ፡ ለመሞቴ ሊያበቃ ፡ ይህ ፡ ታሪኬ ጀንበር ፡ ልትጠልቅ ፡ አዘቅዝቃ ያለኝ ፡ ተስፋ ፡ ሊያበቃ ፡ ሲል እጁ ፡ መጣ (፬x) ጌታ ፡ መጣ (፬x) እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x) ለብዙ ፡ ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ ጦር ፡ ከጁ ፡ ያልተለየው ወርውሮ ፡ ወርውሮ ፡ የማይስተው ፡ ሳኦል ፡ የተባለው ዳዊት ፡ ላይ ፡ ወርውሮ ፡ ለምንድነው ፡ የሳተው አዝኖለት ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋርዶት ፡ ነው (፪x) የዚህ ፡ አለም ፡ ገዢ ፡ በጥልቅ ፡ ተቀምጦ ሲፎክር ፡ አየሁት ፡ የእኔ ፡ አይኔ ፡ ተከፍቶ ሲፎክር ፡ ሰምቼ ፡ ልቤ ፡ ሲርድብኝ ጌታ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እኔን ፡ ተናገረኝ የፉከራ ፡ ድምፁን ፡ ሰምተህ ፡ ከምትፈራ የተፃፈለትን ፡ ሂድ ፡ እና ፡ አንብበው ቅዱሱን ፡ መጽሐፍ ፡ ገልጬ ፡ ሳነበው የወንድሞች ፡ ከሳሽ ፡ ተጥሏል ፡ ነው ፡ እሚለው እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x) የጠላቴ ፡ ውጥኑ ፡ እቅዱ ተስፋ ፡ ያረገው ፡ ክፉ ፡ ወጥመዱ ባዶ ፡ ውሎ ፡ ባዶ ፡ አደረ በአምላኬ ፡ እቅድ ፡ ተሰበረ ያሰበው ፡ አልተሳካም ፡ ያሰበው (፬x) ጳውሎስ ፡ ከባህር ፡ ላይ ፡ ከመርከብ ፡ አደጋ ወደዳሩ ፡ ደርሶ ፡ እንደተረጋጋ ብርድ ፡ ስለነበር ፡ እሳት ፡ እየሞቀ ድንገት ፡ ከእጁ ፡ ላይ ፡ በእባብ ፡ ተነደፈ ካሁን ፡ ካሁን ፡ አብጦ ፡ ይሞታል ፡ እያሉ እዛው ፡ ይቀበራል ፡ ፡ ብለው ፡ ሲወያዩ በእርጋታ ፡ መንፈስ ፡ እባቡን ፡ አራግፎ ጌታን ፡ አገልግሏል ፡ ከእፉኝት ፡ ተርፎ እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x) ለብዙ ፡ ለብዙ ፡ ዘመናት ፡ ጦር ፡ ከጁ ፡ ያልተለየው ወርውሮ ፡ ወርውሮ ፡ የማይስተው ፡ ሳኦል ፡ የተባለው ዳዊት ፡ ላይ ፡ ወርውሮ ፡ ለምንድነው ፡ የሳተው አዝኖለት ፡ አይደለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ጋርዶት ፡ ነው (፪x) እጁ ፡ መጣ ፡ ጌታ ፡ መጣ (፬x)