Loading
Singer
እኔማ ፡ አለኝ ፡ ክብር (፪x) እኔማ ፡ አለኝ ፡ አክሊል (፪x) ለጽዮን ፡ ስብሰባ ፡ ተጠርቻለሁ ስራው ፡ በእኔ ፡ ተቆጥሮ ፡ ትገቢያለሽ ፡ ተብያለሁ ኩነኔ ፡ የለብኝም ፡ ከሳሼስ ፡ ማነው እርሱ ፡ በደሙ ፡ አጽድቆ ፡ ልጁ ፡ ተብያለሁ ከግብጽ ፡ ምድር ፡ ቢወጡ ወደ ፡ ተስፋይቱ ፡ ምድር ወደ ፡ ውቧ ፡ ከነዓን ፡ ቢጠሩ ብዙዎቹ ፡ ቀሩ ፡ ምድረ-በዳ ሳይደርሱ ፡ ሳይገቡ ፡ ከእርስታቸው/ከግባቸው ፡ ጋር ያ ፡ ተስፋ ፡ ከፊቴ ፡ ካለው ፡ ጋራ ፡ ፍጹም ፡ አይወዳደር የኔማ ፡ አዲሲቱ ፡ ነው ፡ እየሩሳሌም በበጉ ፡ ቅኔ ፡ በሙሴ ፡ ዜማ እዘምራለሁ ፡ ከመላዕክት ፡ ጋራ ክበር ፡ ክበር ፡ እያልኩ ፡ ፊቱ ፡ እቆማለሁ እርሱ ፡ ስለረዳኝ ፡ እኔ ፡ እዘምራለሁ እሄዳለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ እጠራለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ ከእነ ፡ አብርሀም ፡ ጋራ ፡ ከእነ ፡ ይስሀቅ ከእነ ፡ እስራኤል ፡ ጋራ ፡ ከእነ ፡ ቅዱሳን እሄዳለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ እጠራለሁ ፡ ልዘምር ፡ ወደላይ ፡ ወደላይ