Loading
Singer
ማዕበሉ ፡ ለምን ፡ ገፋኝ ፡ አልልም ፡ ይግፋኝ ወጀቡ ፡ ለምን ፡ ነካኝ ፡ አልልም ፡ ይንካኝ (፪x) አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x) ሁሉን ፡ ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ (፫x) የነፍሴ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ ይችላል ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x) ድንጋዩን ፡ ሁሉ ፡ እንቅፋቱን ከፊቴ ፡ ጠርጐ ፡ ተራራውን በእኔ ፡ ችሎ ፡ የማልችለውን አለማምዶኛል ፡ ተዐምራቱን (፪x) ማቆም ፡ ይችላል ፡ ማዕበሉን ማዘዝ ፡ ይችላል ፡ ንፋሳቱን ባያቆመውም ፡ አውራቂሱን እሻገራለሁ ፡ ይዤ ፡ ቃሉን (፪x) ቁዘማውን ፡ ይውሰደው እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ (፪x) አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x) የሚሆንለት ፡ እርሱ ፡ እንዳለው የሚቆምለት ፡ እንዳሰበው የዕድሜህን ፡ ቁጥር ፡ የሚያሰላው የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ የእኔም ፡ ነው (፪x) ስለዚህ ፡ ለምን ፡ ሽንፈትን ፡ ላውራ ለትንሽ ፡ ነገር ፡ እንደተጠራ ልታመን ፡ እንጂ ፡ ኃይል ፡ ባለው ስሙ ፡ እግዚአብሔር ፡ በተባለው (፪x) ቁዘማውን ፡ ይውሰደው እርሱ ፡ የጠላቴ ፡ ንብረት ፡ ነው ሞት ፡ አይሆንም ፡ በሕይወቴ ገልብጦታል ፡ መድሃኒቴ (፪x) አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x) ኦሮምኛ . (3) . አዝ፦ የአባቶቼ ፡ አምላክ ፡ ትናንት ፡ የረዳኝ ዛሬም ፡ ነግሮኛል ፡ እንደሚያሻግረኝ እሄዳለሁ ፡ ማነው ፡ የሚያቆመኝ እደርሳለሁ ፡ አውሬው ፡ ሳይበላኝ (፪x)