Loading
Singer
ነገ ፡ በሕይወትህ ፡ ድንቅ ፡ አደርጋለሁ ብቻ ፡ አንተ ፡ ተቀደስ ፡ እኔ ፡ ሰራለሁ ብሎ ፡ ጌታ ፡ አሰበኝ ፡ ቃሉን ፡ አክብሮ ምርኮዬን ፡ መልሷል ፡ ስሜን ፡ ቀይሮ አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል ጌታውን ፡ ተማምኖ ፡ የሚጠባበቅ ኃይሉ ፡ ታደሰ ፡ እንጂ ፡ ዘላለም ፡ አይወድቅ እግዚአብሔር ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያረኩት ጸሎቴን ፡ መልሷል ፡ ኑ ፡ ስሙን ፡ ባርኩት አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል በለስን ፡ ጠብቆ ፡ ፍሬን ፡ የበላ ከጌታው ፡ ጋር ፡ ሆኖ ፡ ያልቀረ ፡ ኋላ አከናውኖልኛል ፡ ምኔን ፡ ልክፈለው የሚል ፡ በዕልልታ ፡ ጌታን ፡ ያክብረው አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል ሥጋዬን ፡ በጥርሴ ፡ እነክሳለሁኝ ቢገድለኝም ፡ እርሱን ፡ እጠብቃለሁኝ ብሎ ፡ ለጠበቀው ፡ ጌታን ፡ በእምነት ሁለት ፡ እጥፍ ፡ መጣ ፡ የኢዮብ ፡ በረከት አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል እረድኤቴና ፡ መድሃኒቴ አከናውኖልኛል ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ በፊቱ ፡ ዘላለሁ ፡ እንደ ፡ እንቦሳ ስላራቀው ፡ ከእኔ ፡ ያንን ፡ አበሳ አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል ልጄ ፡ ልብህን ፡ ስጠኝ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ና እሰራለሁ ፡ ብሎ ፡ አባበለና እኔም ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር ፡ ወዲያው ፡ ስታረቅ ጸሎቴን ፡ መለሰው ፡ ሥሙ ፡ ይባረክ አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ጠብቄ ፡ አላፈርኩኝም ምርኮዬም ፡ ተወስዶ ፡ በዛው ፡ አልቀረም በጊዜው ፡ ኢየሱስ ፡ መልሶልኛል ሥሙ ፡ ይባረክ ፡ ይንገሥ ፡ አሰኝቶኛል (፪x)