Loading
Singer
ለሥጋዊ ፡ ነገር ፡ እራስን ፡ ማስለመድ ከእግዚአብሔር ፡ ሀሳብ ፡ እርቆ ፡ መራመድ ለጊዜያዊ ፡ ደስታ ፡ ነፍስን ፡ አስገዝቶ ዛሬን ፡ ብቻ ፡ መኖር ፡ የነገውን ፡ ትቶ አይጠቅመኝም ፡ ከቶ ፡ ይህን ፡ አውቄዋለሁ እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሬያለሁ ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው በሰው ፡ ወግ ፡ ተይዞ ፡ በይሉኝታ ፡ እስራት ዛሬን ፡ ላያሻግር ፡ ለእንጀራ ፡ መገዛት እውነትን ፡ ከመግለጥ ፡ በውሸት ፡ ከልሎ መምሰል ፡ የሌለበት ፡ የማስመሰል ፡ ኑሮ አይጠቅመኝም ፡ ከቶ ፡ ይህን ፡ አውቄዋለሁ እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሬያለሁ ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው ታላቅና ፡ ክቡር ፡ ሕይወትም ፡ የሆነ ከአማራጮች ፡ ሁሉ ፡ እጅግ ፡ የተሻለ አሁን ፡ ላለውና ፡ ለመጪው ፡ ዘመኔ እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ያዋጣኛል ፡ ለእኔ ያዋጣኛል ፡ አዎ ፡ ይህን ፡ አውቄያለሁ እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሪያለሁ ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው ከኋላ ፡ ያለውን ፡ በሙሉ ፡ ረስቼ የፊቴን ፡ ለመያዝ ፡ እጆቼን ፡ ዘርግቼ ምልክት ፡ አይቼ ፡ መፍጠን ፡ ጀምሬያለሁ መጠራቴ ፡ ዋጋው ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሬያለሁ እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው ስለዚህ ፡ የሚይዘኝ ፡ የሚያስቀረኝ ፡ ማነው ሁሉንም ፡ እየጣስኩ ፡ ወደፊት ፡ ሄዳለሁ