Loading
Singer
አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት? ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት ዝም ፡ ያሰኘለት? ተራራ ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ጠላቴ ፡ ሲፎክር የማይወድቅ ፡ መስሎት ፡ ሕይወቴን ፡ ሲያሸብር በሰማይ ፡ የሚኖር ፡ አምላክ ፡ የሆነው ከከፍታ ፡ አውርዶ ፡ በእግሬ ፡ ሥር ፡ ጣለው አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት? ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት ዝም ፡ ያሰኘለት? ዘወትር ፡ ዕንቅፋትን ፡ በፊቴ ፡ ላይ ፡ ሲያኖር ከበነዋል ፡ በቃ ! እያለ ፡ ሲፎክር መብረቁን ፡ ልኮ ፡ ጌታ ፡ አወካቸው ዳግም ፡ ላይነሱ ፡ በጥልቅ ፡ ጣላቸው አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት? ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት ዝም ፡ ያሰኘለት? ነበረብኝ ፡ ብዙ ፡ ሸክም ፡ የሆነብኝ ልቤንም ፡ አቅልጦት ፡ በጣም ፡ ያስጨነቀኝ ጌታ ፡ ደርሶልኝ ፡ እኔን ፡ አስጥሎኛል በቅዱሱ ፡ ማደሪያው ፡ እንዳርፍ ፡ እረድቶኛል አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት? ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት ዝም ፡ ያሰኘለት? እንደዚህ ፡ እረድቶኝ ፡ ከጠላት ፡ ድኛለሁ በማያልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ ጸንቼ ፡ ቆሜያለሁ ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ ጌታ ፡ ይቀድመኛል ስለሚዋጋልኝ ፡ ማክበር ፡ ይገባኛል አዝ፦ ማነው ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ የተዋጋለት? ከፊቱ ፡ ወጥቶ ፡ ጠላትን ፡ ሁሉ ፡ ድል ፡ የነሳለት ዝም ፡ ያሰኘለት?