Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ የታል ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ ፍጥረታት ፡ በዙሪያህ ፡ ከበውህ ፡ እያየህ ዓይን ፡ አጥርቶ ፡ ቢያይ ፡ ጆሮችህ ፡ ቢያቀኑ የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ታይ ፡ ነበር ፡ በውኑ ውጣ ፡ ወደ ፡ ሜዳው ፡ ሂድ ፡ ወደ ፡ ሃይቁ የፍጥረትን ፡ ሰሪ ፡ ቢያሻህ ፡ መጠየቁ አቀበቱን ፡ ውጣ ፡ ቁልቁለቱን ፡ ውረድ ሜዳ ፡ ለጥ ፡ ያለውን ፡ ወይ ፡ ረዥሙን ፡ መንገድ በደረስክበቱ ፡ የሰማህ ፡ ያየኸው ሰሪና ፡ ተካዩ ፡ ሕያው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው እያት ፡ ቢራቢሮ ፡ ተፈጥሮ ፡ ያስጌጣት ክንፎቹዋ ፡ ርግብግብ ፡ ውበት ፡ የተሰጣት ተመልከት ፡ ወፊቱን ፡ ጐጆ ፡ ስትራ መሰረቱን ፡ ጥላ ፡ ለፍታ ፡ ጥራ ፡ ግራ የትም ፡ ዞራ ፡ ዞራ ፡ በአየር ፡ በደመና ተመልሳ ፡ ቤቷ ፡ ሳትስት ፡ ጐዳና አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ እግዚአብሔር ፡ የታል ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ ፍጥረታት ፡ በዙሪያህ ፡ ከበውህ ፡ እያየህ ዓይን ፡ አጥርቶ ፡ ቢያይ ፡ ጆሮችህ ፡ ቢያቀኑ የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ታይ ፡ ነበር ፡ በውኑ ነፋሱም ፡ ያፏጫል ፡ ዛፉም ፡ ይራወጣል ጂረቱም ፡ ይፈሳል ፡ ምንጩም ፡ ያው ፡ ይፈልቃል ቀን ፡ ለፀሐይ ፡ መውጫ ፡ ማታው ፡ ለጨረቃ ጨለማና ፡ ብርሃን ፡ በተራ ፡ ጥበቃ ወቅት ፡ ሲፈራረቅ ፡ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ እግዚአብሔር ፡ ያውልህ ፡ እየው ፡ በፍጥረቱ ከፀሐይ ፡ ባሻገር ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ርቀት እልፍ ፡ አእላፍ ፡ ክዋክብት ፡ ያሸበረቀበት ዓሣ ፡ ነባሪውም ፡ በውቂያኖስ ፡ ጥልቀት አናብስቱ ፡ በዱር ፡ ሲያገሱ ፡ በርቀት ገብረ ፡ ጉንዳን ፡ ሰልፉ ፡ ሁከት ፡ የሌለበት ውብ ፡ ፍጥረት ፡ ዙሪያህን ፡ አልመጣ ፡ እንደድንገት አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ