Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው እንዲህ ፡ አለው (፫x) "አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ? በዘሩባቤል ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ" አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው ከእንግዲህስ ፡ ምን ፡ ሊበጀኝ ፡ እዬዬ ፡ ማለት ፡ ሰለቸኝ አይደርሰኝም ፡ ወይ ፡ ወረፋ ፡ አይገድህም ፡ ወይ ፡ ስጠፋ አምላካዊ ፡ መልስ ፡ ከሰማይ ፡ ዘሎ ፡ በኮረብታዎች ፡ ላይ ዙሪያ ፡ ገባውን ፡ አበራው ፡ ተገፈተረ ፡ ተራራው አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው እንዲህ ፡ አለው (፫x) "አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ? በልጄ ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ" አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው Yedura ሜዳ ፡ ሃውልቱ ፡ ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ነዶ ፡ እሳቱ ሊያጠፋኝ ፡ የተመኘው ፡ ጌታ ፡ በቁጣው ፡ ጐበኘው ጠላት ፡ ለራሱ ፡ ቆፈረ ፡ ሊያስረኝ ፡ የወጣው ፡ ታሰረ ሊበላኝ ፡ ያሻው ፡ ተበላ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ በተድላ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው እንዲህ ፡ አለው (፫x) "አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ? በልጄ ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ" አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው የብዙ ፡ ዘመን ፡ ጠላቴ ፡ ቆሞ ፡ የነበረ ፡ በፊቴ ብርሃን ፡ እንዳላይ ፡ ከልሎ ፡ አየሁ ፡ በጌታዬ ፡ ተጥሎ ጌታ ፡ በሰራው ፡ ከበረ ፡ መዝሙር ፡ በአፌ ፡ ጨመረ ሰማይ ፡ ያጨብጭብ ፡ በደስታ ፡ ምድር ፡ ታክብረው ፡ በእልልታ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው እንዲህ ፡ አለው (፫x) "አንተ ፡ ተራራ ! ኧረ ፡ ለመሆኑ ፡ ምንድነህ? በዘሩባቤል ፡ ፊት ፡ ደልዳላ ፡ ሜዳ ፡ ትሆናለህ" አለው (፫x) ፡ ናደው ፡ ደለደለው