Loading
Singer
ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ለክብሩ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው ትልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ለኃይሉ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው (፪x) እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ የክብሩን ፡ ብዛት ፡ ግርማውን ፡ እያየሁ እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ የኃይሉን ፡ ችሎት ፡ ብርታቱን ፡ እያየሁ (፪x) በጠባባ ፡ አይምሮዬ ፡ አልችልም ፡ ልገምተው እስካሁን ፡ ካወቅሁት ፡ በላይ ፡ እግዚአብሔር ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነው እንኳን ፡ ማንነቱ ፡ ቀርቶ ፡ ስራውም ፡ አይመረመር ከተባለው ፡ ሁሉ ፡ ያልፋል ፡ ይበልጣል ፡ የአምላኬ ፡ ክብር በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልናገር በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልመስክር ቃላት ፡ ባጣም ፡ እንዲያው ፡ ላመስግነው አምልኮዬ ፡ እርሱን ፡ ባይመጥነው (፪x) ግርማው ፡ እጅግ ፡ የሚያስፈራ ፡ ታላቅ ፡ ስሙ ፡ የገነነ ደግሞ ፡ መሃሪ ፡ ቸር ፡ አምላክ ፡ የፍቅር ፡ ጌታ ፡ የሆነ ብርሃንን ፡ ተጐናጽፎ ፡ ማደሪያውን ፡ በክብር ፡ የሞላ እንደእግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ አምላክስ ፡ የታለ ፡ ሌላ ትልቅ/ታላቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ/ታላቅ ፡ ነው ለክብሩ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው ታልቅ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ታልቅ ፡ ነው ለኃይሉ ፡ መጨረሻ ፡ የሌለው (፪x) እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ የክብሩን ፡ ብዛት ፡ ግርማውን ፡ እያየሁ እዘምራለሁ ፡ ለእርሱ ፡ እቀኛለሁ የኃይሉን ፡ ችሎት ፡ ብርታቱን ፡ እያየሁ (፫x) በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልናገር በምን ፡ ቋንቋ ፡ ስለእርሱ ፡ ልመስክር ቃላት ፡ ባጣም ፡ እንዲያው ፡ ላመስግነው አምልኮዬ ፡ እርሱን ፡ ባይመጥነው (፪x)