Loading
ችግር ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሙላትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም ጭንቀት ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከሰላምህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም ድካም ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከጉልበትህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም ማጣት ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ከዙፋንህ ፡ ፊት ፡ ሲቆም ይሟሟሉ ፡ ይቀልጣሉ ፡ መገኘትህን ፡ ሲረዱ የከበዱት ፡ ዙፋን ፡ ስጡኝ ፡ ያሉ ለቀው ፡ ሄዱ ፡ እያፈሩ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ትልቅ (፬x) ከተራራው ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከከበደው ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከነገሩኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከችግሩ ፡ በላይ ፡ ትልቅ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ (፬x) ከጨነቀኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከነገሩኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከሰበክነው ፡ በላይ ፡ ትልቅ ካመለኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ የሰልፉ ፡ አለቃ ፡ ብቻህን ፡ ምትገዛ ምድርን ፡ ፍጥረትን ፡ በቃልህ ፡ ያጸናህ (፪x) ዕድሜ ፡ ማይወጣልህ ፡ ኃይልህ ፡ አይለካ ምሽግ ፡ መጠለያ ፡ ክንድህ ፡ የበረታ (፪x) ገብተህ ፡ በእኔ ፡ ጓዳ (፪x) ኧረ ፡ ለምን ፡ ልፍራ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ትልቅ ፡ (፬) ከጨነቀኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከነገሩኝ ፡ በላይ ፡ ትልቅ ከሰበክነው ፡ በላይ ፡ ትልቅ ካመለኩት ፡ በላይ ፡ ትልቅ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.