Loading
Singer
ከአፌ ፡ የወጣው ፡ ቃል ፡ ምንም ፡ ሳያፈራ ከቶ ፡ አይመለስም ፡ ሥራውን ፡ ሳይሰራ [1] ብሎ ፡ የተናገረው ፡ ለሥሙ ፡ የሚቀና ገና ፡ አሁን ፡ እናያለን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ (፪x) እንደነቃልን ፡ እንደነቃልን እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ ፡ በዓይናችን ፡ እያየን (፪x) በዓይናችን ፡ እያየን (፬x) ይህ ፡ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ ማንስ ፡ ያውቅበታል ያስ ፡ እንደምን ፡ ሆኖ ፡ ወደዚህ ፡ ይደርሳል በመንፈሱ ፡ እንጂ ፡ በኃይል ፡ የማይሆነው የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ ሁሌም ፡ ፍጻሜ ፡ አለው (፪x) እንደነቃልን ፡ እንደነቃልን እግዚአብሔር ፡ ሲሰራ ፡ በዓይናችን ፡ እያየን (፪x) በዓይናችን ፡ እያየን (፬x) እግዚአብሔር ፡ የሚያስመካ የሚያስደንቅ ፡ የሚያኮራ ሥራው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ሲሰራ ሥራው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ሲሰራ (፪x) የሚታመን ፡ በአንተ ፡ ይታመን የሚመካ ፡ በአንተ ፡ ይመካ የሚደገፍ ፡ በአንተ ፡ ይደገፍ የሚኮራ ፡ በአንተ ፡ ይኩራ እኛስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ ይለናል ፡ ይለናል (፪x) በአንተ ፡ መደገፉ ፡ ያስመካናል (፪x) የአንተ ፡ መሆናችን ፡ ያስመካናል (፪x) እኛስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ ይለናል ፡ ይለናል (፪x) በአንተ ፡ መደገፉ ፡ ያስመካናል (፪x) በአንተ ፡ መታየቱ ፡ ያስመካናል (፪x) በአንተ ፡ መደገፉ ፡ ያስመካናል (፪x) በአንተ ፡ መታየቱ ፡ ያስመካናል (፪x)