Loading
Singer
የሚገርመኝ ፡ እኔ ፡ ቅጥሩ ፡ ታላቅ ፡ ነው ማንም ፡ እንዳይነካኝ ፡ ለእኔ ፡ ያሰበው ተዘልለሽ ፡ ኑሪ ፡ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ ለምን ፡ ትፈሪያለሽ ፡ . (1) . አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ሰማሁ ፡ ተነሳሁ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ ሰላም ፡ ኑሪ ፡ አለኝ (፪x) እኔን ፡ የሚጠብቅ ፡ አይተኛ ፡ አያንቀላፋ ይልቁን ፡ በእሳቱ ፡ ጠላቴን ፡ አጠፋ ክንዱ ፡ ተዘርግታ ፡ አርፌ ፡ በጌታ ሳልሰጋ ፡ ኖራለሁ ፡ ሁልጊዜም ፡ በደስታ እርግማን ፡ እንዳይሰራ ፡ በዘመኔ ሟርትም ፡ እንዳይሰራ ፡ በዘመኔ ቅጥር ፡ ሆንከኝ ፡ መድህኔ (፫x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ሰማሁ ፡ ተነሳሁ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ ሰላም ፡ ኑሪ ፡ አለኝ (፪x) የጠላቴን ፡ ምክር ፡ ዛቻውን ፡ እንዳልፈራ በእሳት ፡ የሚመልስ ፡ አለኝ ፡ የሚያኮራ ዙሪያዬ ፡ ቢዞር ፡ ጠላት ፡ ቢጮህ መናወጥ ፡ አላውቅ ፡ ሰላሜ ፡ አይጠፋ እግዚአብሔር ፡ ብሎኛል ፡ ልጄ ፡ እረፊ በዘመንሽ ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ ለአንቺ ሰላም ፡ ይሁን ፡ ከቤትሽ (፫x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ሰማሁ ፡ ተነሳሁ እኔ ፡ ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነኝ ሰላም ፡ ኑሪ ፡ አለኝ (፪x)