Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው ፡ በሥጋም ፡ አይደፈር እጅግም ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ በሰው ፡ የማይገመት ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ክንዱ ፡ ኃያል ፡ ያደርጋል ቢወዱም ፡ ቢጠሉም ፡ ኢየሱስ ፡ ይነግሣል አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሥሙን ፡ በመታመን ፡ ሲቀርቡት ፡ ይቀርባል በደከመች ፡ ሕይወት ፡ ብርታት ፡ ይጨምራል ሞገዱን ፡ ፀጥ ፡ አድርጐ ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል ምንጩን ፡ አጠጥቶ ፡ በረሃን ፡ ያለማል አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የማይታየው ፡ ባህሪ ፡ የዘላለም ፡ ኃይሉ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ በእውነት ፡ ሲያስተውሉ ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ ከተሰሩት ፡ ደምቆ ይኖራል ፡ ኢየሱስ ፡ ህልውናው ፡ ታውቆ አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የተዓምራት ፡ አምላክ ፡ ክንዱ ፡ መች ፡ አጠረ ሰው ፡ ያወቀ ፡ መስሎት ፡ ብዙ ፡ የመረመረ ኃጢአትን ፡ አጣጥሞ ፡ ለፍርድ ፡ እየኖረ ጌታን ፡ የለም ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ አጣመረ አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው