Loading
Singer
Updated 10h ago
በሕይወቴ ፡ ያለፈውን ፡ ዞር ፡ ብይ ፡ ሳየው ፡ ስመለከተው የእኔ ፡ ጉልበት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ መልካምነቱ ፡ ነው የእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ጌታ ፡ ነው አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x) የሚመስለው ፡ ማነው በመልካምነቱ ፡ በመልካምነቱ ፡ ታጋሽ ፡ ርህሩህነቱ ነገሬ ፡ የሰመረው (፫x) ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x) ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፬x) የእራሴ ፡ አስተዋፅዖ ፡ አንድም ፡ የሌለበት ያልደከምኩበት ፡ እዚህ ፡ ለመድረሴ ፡ ምክንያቱ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ እግዚአብሄር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x) የሚመስለው ፡ ማነው በመልካምነቱ ፡ በመልካምነቱ ፡ ታጋሽ ፡ ርህሩህነቱ ነገሬ ፡ የሰመረው (፫x) ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x) ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፬x) በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ሳይኖር ምንጭን ፡ አፈለቀ ፡ ጌታ ፡ በተዓምር የምድረ ፡ በዳዉ ፡ ሃሩር ፡ ሳያገኘኝ የነ ፡ ሙሴ ፡ አምላክ ፡ ተጠነቀቀልኝ ወጥመድ ፡ ተሰበረ ፡ ወጥመድ ፡ ተሰበረ ጌትዬ ፡ ከበረ ወጥመዱን ፡ ሲሰብረው ፡ ወጥመዱን ፡ ሲሰብረው ባይኔ ፡ አይቻለሁ በሕይወቴ ፡ ያለፈውን ፡ ዞር ፡ ብይ ፡ ሳየው ፡ ስመለከተው የእኔ ፡ ጉልበት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ መልካምነቱ ፡ ነው የእኔ ፡ ብርታት ፡ ሳይሆን ፡ እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ኧረ ፡ እሱ ፡ ጌታ ፡ ነው አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (፪x) የሚመስለው ፡ ማነው በመልካምነቱ ፡ በመልካምነቱ ፡ ታጋሽ ፡ ርህሩህነቱ ነገሬ ፡ የሰመረው (፫x) ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፪x) ከኢየሱስ ፡ የተነሳ ፡ ነው (፬x)