Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x) በወይን ፡ ሐረግ ፡ ዘንድ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ ባይኖር ፡ የሚረዳ ፡ ከግራ ፡ ከቀኝ በለሷን ፡ ጠብቄ ፡ ፍሬን ፡ እበላለሁ ቀኝ ፡ እጄን ፡ የያዘኝ ፡ መቼ ፡ ሊረሳኝ ፡ ነው እሱን ፡ ታምኖ ፡ ጠርቶ ፡ ከቶ ፡ ማንስ ፡ አፍሯል ይልቁን ፡ በስሙ ፡ ቀንዱ ፡ ከፍ ፡ ብሏል እኔም ፡ በስሮቼ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ እላለሁ አለኝ ፡ የሚረዳ ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ (፫x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x) ጨለማው ፡ በርትቶ ማይነጋ ሲመስል ዮርዳኖስም ፡ ሞልቶ ፡ አላሻግርም ፡ ሲል ታምራት ፡ አድርጎ ፡ ያሻገረው ፡ ጌታ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ በእኔ ፡ ቦታ ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ድል ፡ የነሳ ፡ ጌታ ሰባቱን ፡ ማህተም ፡ ተርትሮ ፡ የፈታ ዛሬም ፡ በቸርነት ፡ ይከታተለኛል እሱን ፡ ተደግፌ ፡ ምንስ ፡ ያሰጋኛል (፫x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ለእኔ (፪x) ሁልጊዜ ፡ በዘመኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ በጐ ፡ ለእኔ (፪x) ወረት ፡ የለበትም ፡ ፍቅሩ ፡ ሁሌ ፡ ስያፈቅር ፡ ይኖራል መንገድ ፡ አስጀምሮ ፡ ጉዞ ፡ መች ፡ እዚህ ፡ አውጥቶ ፡ ይሄዳል እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ አርጎ ፡ ይዞ ፡ በብዙ ፡ ሞገስ ፡ ያኖራል ላይተው ፡ ላይረሳ ፡ በራሱ ፡ በስሙ ፡ ኪዳን ፡ ይምላል (፪x)