Loading
Singer
Updated 8/4/2026
ብዙ ፡ ተዓምራቶችን ፡ ሲሰራ ፡ ያያችሁ ሁልጊዜ ፡ በቃሉ ፡ እንዲህ ፡ ሲናገራችሁ ማነው ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ/ጌታ ፡ የሚሆንላችሁ በመከራው ፡ ጌዜ ፡ ከእርሱ ፡ የሸሻችሁ (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና ቅዱሳኖች ፡ ጽኑ ፡ ጨለማው ፡ ይነጋል ኢየሱስ ፡ ሲያስበን ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል ፀሐይ ፡ ሲወጣበት ፡ ተኖ ፡ እንደሚጠፋ ቀናችን ፡ ይሄዳል ፡ ያስቆረጠን ፡ ተስፋ (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና እግዚአብሔር ፡ ከልቡ ፡ አያስጨንቀንም ሕዝቡን ፡ ለተኩላዎች ፡ አሳልፎ ፡ አይሰጥም ቢያሳዝነን ፡ እንኳን ፡ ልቡ ፡ ሚራራ ፡ ነው ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ መስማማት ፡ ያ ፡ ነው ፡ የሚሻለው (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና ክለቅሶ ፡ ከሃዘን ፡ ከማማረር ፡ ሕይወት ክውድቀት ፡ ከድካም ፡ ፈጥኖ ፡ ሚያነሳበት የጠፉትን ፡ ሁሉ ፡ የሚፈልግበት እግዚአብሔር ፡ ጊዜ ፡ አለው ፡ የሚጐብኝበት (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ማንንም ፡ ጥሎ ፡ አያውቅምና ቸርነት ፡ ምህረቱ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋር ፡ ነውና የመረጠህ ፡ አምላክ ፡ አይተውህምና አንተም ፡ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ ጽና (፪x)