Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ ኃያል በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x) ህዝቡን ፡ ከልሎ ፡ የሚዋጋ ለጠላት ፡ ዛቻ ፡ የማይሰጋ ብድራትን ፡ መላሽ ፡ የእኛ ፡ አምላክ ይርታ ፡ እንጂ ፡ መረታትን ፡ አያውቅ(፪x) እግዚአብሔር ፡ ኃያል በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x) የእምነት ፡ ባለድል ፡ ሳይጸጸት ጌታውን ፡ አምኖ ፡ ሳያፍርበት ለተስፋው ፡ ለብሶ፡ ሰንሰለት ሕይወቱን ፡ ሰጥቷል ፡ ሳይሰስት(፪x) እግዚአብሔር ፡ ኃያል በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x) አንተም ፡ በኃይሉ ፡ ድል ፡ ነስተህ በእቶን ፡ ተፈትነህ ፡ ነጥረህ ለመንግሥቱ ፡ ብቁ ፡ ሆነህ እንድትወጣ ፡ ጌታ ፡ ይርዳህ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ኃያል በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x) ያን ፡ ጊዜ ፡ ተዋግቶ ፡ የረታ የጠላቱን ፡ ጅማት ፡ የፈታ በፅኑ ፡ አመታት ፡ የሚመታ ሁሉን ፡ የሚችል ፡ የድል ፡ ጌታ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ኃያል በሰልፍም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x)