Loading
Singer
ከምናስበው ፡ ከምንገምተው ፡ ክምናውቀውም ፡ በላይ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ድንቅ ፡ ነው ማን ፡ ይመስለዋል ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ሊቀረብ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ ነው ከእርሱ ፡ በፊት ፡ አምላክ ፡ አልተሰራም ፡ ከእርሱ ፡ በሃላም ፡ ማንም ፡ ዓይኖርም ከእግዚአብሔር ፡ ሌላ ፡ የሚያድን ፡ የለም ባሕርን ፡ ከፍሎ ፡ መንገድ ፡ ያደርጋል በምድረ ፡ በዳ ፡ ከአለት ፡ ውኃ ፡ ያፈልቃል በደረቅ ፡ በርሃ ፡ መናን ፡ ይመግባል ሸለቆውንም ፡ ውኃ ፡ ይሞላል እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ሁሉን ፡ ይችላል ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በቃሉ ፡ ፈጥራል ከዋክብቶችን ፡ በስማቸው ፡ ይጥራል የጸጉራችን ፡ ቁጥር ፡ በእርሱ ፡ ተቆጥራል ልብን ፡ ኩላሊትን ፡ ይመረምራል እግዚአብሔር ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ እርሱ ፡ አምላክ ፡ ነው እንደርሱ ፡ ያለ ፡ የለም ፡ እግዚአብሔር ፡ ልዪ ፡ ነው ፡ ክሰው ፡ አእምሮ ፡ ከዕውቀቱ ፡ በላይ ፡ ነው በምድር ፡ በሰማይ ፡ የተፈራ ፡ ነው ከሁሉም ፡ ነገር ፡ በላይ ፡ ነው