Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን (፬x) በምድር ፡ ሰልፍ ፡ ሲያይል ፡ ሲበረታ ያመኑትም ፡ ቃልኪዳኑ ፡ ሲፈታ መውጫው ፡ ጠፍቶ ፡ ቀኑ ፡ ሲጨላልም መባረኪያው ፡ ዘመኑ ፡ ሲረዝም ጌታን ፡ ታምኖ ፡ በአንዳች ፡ ሳይጨነቅ በወጀቡ ፡ ፈርቶ ፡ ስፍራን ፡ ሳይለቅ ማን ፡ ነው ፡ እርሱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ያረፈ መከራውን ፡ በደስታ ፡ ያለፈ (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን እናምናለን ፡ ይሄን ፡ እናምናለን (፫x) በአንበሶች ፡ ጉድጓድ ፡ መጣል ፡ መርጦ የአንብን ፡ ማስፈራራት ፡ ረግጦ ከልቡ ፡ ነው ፡ ለአምላክ ፡ ያደረሰው ብርቱ ፡ ነፋስ ፡ ያላንገዳገደው አልበላው ፡ አውሬው ፡ አንደዋዛ በክብሩ ፡ ያ ፡ ሰው ፡ ተገዛ ቢመስል ፡ እንኳን ፡ እግዚአብሔር ፡ የጣለው የሚሆነው ፡ ሁሉም ፡ ለበጐ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን (፪x) እንሰብካለን ፡ ይሄን ፡ እንሰብካለን (፪x) ቢያሰለችም ፡ የምድር ፡ ውጣ ፡ ውረድ ሌላው ፡ ሲከብር ፡ አንተ ፡ ብትዋረድ ብርሃኑ ፡ ቶሎ ፡ ቢመሽብህ የታመንከው ፡ ድንገት ፡ ቢርቅብህ ያስብሃል ፡ ጌታ ፡ በሞገሱ አካሎችህ ፡ መከራ ፡ እስኪረሱ አትከፋ ፡ በአምላክ ፡ ፀጋ ፡ ቻለው አይጥልህም ፡ እግዚአብሔር ፡ ቀን ፡ አለው (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእውነት ፡ ለሚወዱ እንደ ፡ ሀሳቡም ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ እናውቃለን ፡ ይሄን ፡ እናውቃለን እንሰብካለን ፡ ይሄን ፡ እንሰብካለን እናምናለን ፡ ይሄን ፡ እናምናለን (፪x)