Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ፩) ፈርኦን ፡ ሊገዛ ፡ እስራኤልን ልቡን ፡ አደንድኖ ፡ ከፍ ፡ ቢልም ሕዝቡን ፡ ለመታደግ ፡ የቆረጠው የሰራዊት ፡ ጌታ ፡ አሸነፈው አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ፪) ዳንኤል ፡ ቢጣልም ፡ በጉድጓዱ አንበሳ ፡ እንዲበላው ፡ ቢታዘዝ የኃያላን ፡ ሀያል ፡ ኢየሱስ አዳነ ፡ ካንበሳው ፡ ባሪያውን አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ፫) መከራ ፡ ቢከበን ፡ ዙሪያችን ተቆረጠ ፡ ስንል ፡ ተስፋችን በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ የሚል ልዑል ፡ አምላካችን ፡ ባለድል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ፬) አይሆንም ፡ ተብሎ ፡ ተቆርጦ ተስፋዬ ፡ በሙሉ ፡ ተሟጦ እግዚአብሔር ፡ ቃሉን ፡ አሰበ ነገር ፡ በጊዜው ፡ ጨኮለ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው ፭) አፍ ፡ ባለው ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ ብሎ በከፍታዎች ፡ ላይ ፡ ድንቅ ፡ ሆኖ የኖረ ፡ ሳይረታ ፡ ዘላለም እግዚአብሔርን ፡ የሚመስል ፡ የለም አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ በከፍታው ፡ ድንቅ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነው