Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ አማሌቅ ፡ በመንገድ ፡ ተቃወመን ደክመን ፡ ሳለን ፡ መንገድ ፡ ዘጋጋብን ተዋጊውእግዚአብሄር ፡ ድል ፡ አድርጎልን ስንት ፡ ጭንቅ ፡ መንገዶችን ፡ አለፍን ተዋጊው ፡ ወዳጄ ፡ ፊት ፡ ቀድሞልን ስንት ፡ ጭንቅ ፡ መንገዶችን ፡ አለፍን አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ እርምጃችንን ፡ ሊያሰናክሉ ፡ የመከሩ የክፋት ፡ ሰራዊት ፡ መጥመድን ፡ ሰወሩ በመንገዳችን ፡ ላይ ፡ እንቅፋት ፡ አኖሩ ጌታ ፡ ደርሶልን ፡ ፈረሰ ፡ ምክሩ (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ ከአውሬ ፡ ጋር ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ታግለናል ስለነፍሳችን ፡ እንኳን ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠናል በብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ መሀል ፡ ክንዱን ፡ አይተናል በአምላካችን ፡ ብርታት ፡ ቅጥሩን ፡ ዘለናል (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ የጨካኞች ፡ ቁጣ ፡ እስትንፋስ ቅጥርን ፡ እንደሚመታ ፡ አውሎንፋስ ባየለበት ፡ ዘመን ፡ በእርሱ ፡ ድል ፡ አድርገናል በክንዱ ፡ ፅናት ፡ ከሁሉ ፡ ተርፈናል (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ብቻውን ፡ መርቶ በፀናች ፡ ክንድ ፡ በድል ፡ ረትቶ የምታስፈራውን ፡ ምድረበዳ ተሸገርን ፡ በጌታ ፡ ሳንጎዳ የፈራናትንም ፡ ምደረበዳ ተሸገርን ፡ በእግዚአብሔር ፡ ሳንጎዳ