Loading
Singer
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ አምባዬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፣ ኢየሱስ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ ኢየሱሴን ፡ ኢየሱሴን ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ (፪x) እርሱ ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስደነግጥም ፡ አድኖኛል እውነት ፡ እንደጋሻ ፡ ሆኖ ፡ ዙሪያዬን ፡ ከቦኛል መድኃኒት ፡ መድኃኒት ፡ እርሱ ፡ ሆኖልኛል (፪x) በቀንም ፡ ከሚበር ፡ ከሌሊትም ፡ ግርማ ፡ አድኖኛል በመንገዴ ፡ ሁሉ ፡ ስለኔ ፡ መላእክቱ ፡ ታዘዋል ጥበቃው ፡ ጥበቃው ፡ እንዴት ፡ ያስተማምናል (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ አንተ ፡ አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ እለዋለሁ አምባዬና ፡ መሸሸጊያዬ ፡ ነው ፣ ኢየሱስ ፡ በእርሱ ፡ እታመናለሁ ኢየሱሴን ፡ ኢየሱሴን ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ (፪x) በተኩላና ፡ በእባብ ፡ ላይም ፡ እጫማለሁ አንበሳ ፡ ዘንዶውን ፡ እረጋግጣለሁ በርሱ ፡ ተማምኜ ፡ ሁሉንም ፡ አልፋለሁ ስሙንም ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ ፡ እጠራለሁ (፪x) ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) ኢየሱስ ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ ፡ ኢየሱስ ኢየሱስ ፡ በጣም ፡ እወደዋለሁ ፡ ኢየሱስ ሃሌሉያ ፡ (፬x)