Loading
Singer
የጭንቁ ፡ ጊዜ ፡ ሳይመጣ ፡ ግዳጅ ፡ ሳይሆንብኝ አመልካለሁ ፡ በውዴታ ፡ አየተገዛሁ ፡ ለጌታ (፪x) ግዴታዬን ፡ ለማክበር ፡ አይደለም ፡ የማመሰግነው ይልቁንም ፡ ፍቅሩ ፡ ጨምሮብኝ ፡ አጣሁኝ ፡ የምለው (፪x) ሳይወዱ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ቢሉት ፡ ቀን ፡ አስገድዷቸው እኔ ፡ አስቲ ፡ ልዘምርለት ፡ ምቹ ፡ ሳለ ፡ ጊዜው (፪x) ስንት ፡ የምለው ፡ ነገር ፡ በልቤ ፡ የለኝ ቃላት ፡ አቅም ፡ አጣ ፡ ተቸገርኩ ፡ እያነሰብኝ እኔ ፡ ከማቀርበው ፡ እልፍ ፡ የምስጋና ፡ ቃል የእግዚአብሔር ፡ የአንድ ፡ ቀን ፡ ምሕረቱ ፡ ይመዝንብኛል የሚያሳስበኝ ፡ እሱን ፡ አንዴት ፡ እንደማከብር ፡ ነው የሚያሳስበኝ ፡ እሱን ፡ አንዴት ፡ እንደማስከብር ፡ ነው የሚያሳስበኝ ፡ ጌታን ፡ አንዴት ፡ እንደማከብር ፡ ነው የሚያሳስበኝ ፡ እሱን ፡ አንዴት ፡ እንደማስከብር ፡ ነው ነገር ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ኑሮም ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፪x) አንዳንድ ፡ ጊዜ ፡ አይደለም ፡ የማመሰግነው ሲጐልም ፡ እሰየሁ ፡ ሲሞላም ፡ እሰየሁ የማመሰግንበት ፡ ምክንያቴ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ካለ ፡ ቤቴ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x) እጠግባለሁ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ (፪x) እሱ ፡ ካለ ፡ ቤቴ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x) እጠግባለሁ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ (፪x) የሚያሳስበኝ ፡ አንተን ፡ አንዴት ፡ እንደማከብር ፡ ነው የሚያሳስበኝ ፡ አንተን ፡ አንዴት ፡ እንደማስከብር ፡ ነው (፪x) አፌን ፡ ሞልቼ ፡ እንድዘምረው የሚጋብዘኝ ፡ ማንነትህ ፡ ነው (፪X) ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይድረስህ ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይኸውልህ ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ ነገር ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ኑሮም ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፫x)