Loading
እግዚአብሔር ፡ አለ ፡ በሰማይ ፡ በላይ ፡ በክብሩ ይገዙለታል ፡ ለእርሱ ፡ ሰማይና ፡ ምድሩ ለማያምኑት ፡ ሞኝነት ፡ ነው ለእኛ ፡ ግን ፡ ሕይወት ፡ ነው ፡ ሃሌሉያ (፪x) እናውጃለን ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ እንመሰክራለን ፡ እኛ ፡ ፈጣሪ ፡ አለ ለምንድነው ፡ ተስፋችን ፡ ነው ለማያምኑት ፡ ግን ፡ ጥፋት ፡ ነው (፪x) ለውጦናል ፡ እኛን ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ በቃሉ ፡ አናምናለን ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ለምንድነው ፡ ሕይወታችን ፡ ነው ለሚጠፉት ፡ ግን ፡ ሞት ፡ ነው (፪x) ሲሰራ ፡ አይተናል ፡ እና ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ፍቅሩንም ፡ ቀምሰናል ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ ፈውስን ፡ በልጁ ፡ አግኝተናል የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ሰጥቶናል (፪x) ክብሩን ፡ አይተናል ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ እንመሰክራለን ፡ እኛ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ መስቀሉን ፡ ለእኛ ፡ ክብራችን ፡ ነው ሕይወት ፡ ሰላማችን ፡ ሃይላችን ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.