Loading
Singer
ዕድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ብሰጠው ፡ አይቆጨኝም በመስቀል ፡ ደሙን ፡ ላፈሰሰልኝ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ንጹህ ፡ ሆኖ ፡ እኔ ፡ ግን ፡ ብቆሽሽ በምድር ፡ ላይ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ በኀጢአት ፡ ብበላሽ መሞት ፡ የሚገባኝ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ብሆን ኢየሱስ ፡ ለብቻዬ ፡ ይመጣልኝ ፡ ነበር አዝ:- እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ ላይ ፈልጌ ፡ አጣሁ ፡ እርሱን ፡ መሳይ ኦ ፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ ቀሪ ፡ ዘመኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ክፉ ፡ አመሌን ፡ አይቶ ፡ ከቶ ፡ ያልሰለቸው አስቸጋሪ ፡ ባሕሪዬ ፡ ልቡን ፡ ያላራደው በፍቅሩ ፡ አሸነፈኝ ፡ የራሱ ፡ አደረገኝ የማይገባኝን ፡ ክብር ፡ አለበሰኝ አዝ:- እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ ላይ ፈልጌ ፡ አጣሁ ፡ እርሱን ፡ መሳይ ኦ ፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ ቀሪ ፡ ዘመኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ዕድሜዬን ፡ በሙሉ ፡ ብሰጠው ፡ አይቆጨኝም በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞቶ ፡ ራሱን ፡ ለሰጠኝ አዋርዳለሁኝ ፡ ሁለንተናዬን ፡ ለእርሱ ዳግም ፡ ወዶኛልና ፡ ኢየሱስ ፡ ንጉሡ የፍቅር ፡ ትርጉም ፡ የገባዉ ኧረ ፡ ማነው ፡ ሚገልጸዉ የአፍቃሩ ፡ ትርጉም ፡ ማነው ፡ እርሱ ኢየሱስ ፡ ያልራራ ፡ ለነፍሱ (፪x) አዝ:- እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ በምድር ፡ ላይ ፈልጌ ፡ አጣሁ ፡ እርሱን ፡ መሳይ ኦ ፡ ስለዚህ ፡ እኔ ፡ አመልካለሁ ቀሪ ፡ ዘመኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው