Loading
Singer
ቤትህን ፡ ሊሰራ ፡ የተመረጠው የተወደደ ፡ ጥበብ ፡ የሞላው (፪x) ክብር ፡ ሲሆንለት ፡ ዝና ፡ ሲተርፈው የአባቶቹን ፡ አምላክ ፡ እንደማያውቀው ጣዖት ፡ አምልኮ ፡ ሞት ፡ ሆነ ፡ ፍጻሜው አዝ፦ ዕድሜዬ ፡ ይለቅልኝ ፡ ቤትህ ይለቅልኝ ፡ በፊትህ ሕይወቴ ፡ ይመርልኝ ፡ ፊትህ ይመርልኝ ፡ በፊትህ ሩጫዬ ፡ እንዳይገታ ጠብቀኛ ፡ የእኔ ፡ ጌታ እኔ ፡ እንዳልሆን ፡ ለእኔው ፡ ጠላቴ ሰውረኝ ፡ ከዓይን ፡ አምሮቴ (፪x) አህያ ፡ ፍለጋ ፡ ተልኮ ፡ ቢወጣ እጣ ፡ ወደቀበት ፡ ህዝብን ፡ እንዲመራ ከፍልስጤማዊ ፡ ነጻ ፡ እንዲያወጣ ደርሶ ፡ ንጉሥ ፡ ሲሆን ፡ ትህትና ፡ አጣ ክፉ ፡ መንፈስ ፡ ያዘው ፡ ከአንተ ፡ መንገድ ፡ ወጣ መውደቂያው ፡ ሆነበት ፡ የጊልቦዓ ፡ ተራራ አዝ፦ ዘመኔ ፡ ይለቅልኝ ፡ ቤትህ ይለቅልኝ ፡ በፊትህ ሕይወቴ ፡ ይመርልኝ ፡ ፊትህ ይመርልኝ ፡ በፊትህ ሩጫዬ ፡ እንዳይገታ ጠብቀኛ ፡ የእኔ ፡ ጌታ እኔ ፡ እንዳልሆን ፡ ለእኔው ፡ ጠላቴ ሰውረኝ ፡ ከዓይን ፡ አምሮቴ (፪x) በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ ዓይናቸው ፡ የበራ ጨከኑ ፡ በሕይወት ፡ ለሰሙት ፡ አደራ ቤታቸውን ፡ ሰጡ ፡ ለወንጌል ፡ አደራ አርበኞች ፡ ሆነዋል ፡ እስሩም ፡ ቢጠና ነገሥታት ፡ ፊት ፡ ቆሙ ፡ ወንጌልን ፡ ሰበኩና ሰማዕት፡ ሆነው ፡ አለፉ ፡ ዋጋ ፡ ተመኑና ድል ፡ ለነሳው ፡ ከሕይወት ፡ አክሊል ፡ ታቀዳጃለህ ድል ፡ ለነሳው ፡ በቤትህ ፡ እንዲኖር ፡ ትሾመዋለህ ጅማሬዬ ፡ እንዳማረልኝ ፡ ፍጻሜዬም ፡ ይስመርልኝ መዝገብ ፡ ላከማች ፡ በሠማይ ፡ ቤትህ ብል ፡ በማይበላው ፡ በሌለበት ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ዕድሜዬ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ (፪x) ድል ፡ ለነሳው ፡ ከሕይወት ፡ አክሊል ፡ ታቀዳጃለህ ድል ፡ ለነሳው ፡ በቤትህ ፡ እንዲኖር ፡ ትሾመዋለህ ጅማሬዬ ፡ እንዳማረልኝ ፡ ፍጻሜዬም ፡ ይስመርልኝ መዝገብ ፡ ላከማች ፡ በሠማይ ፡ ቤትህ ብል ፡ በማይበላው ፡ በሌለበት ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ዕድሜዬ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ሕይወቴ ፡ ይመር ፡ እፊትህ ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ውበቴ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ዕድሜዬ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ