Loading
Singer
አዝ:- እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (፪x) እድለኛ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እድለኛ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ለአምልኮ ፡ ማን ፡ ይቀድመኛል መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ የተሰራልኝ ስሞት ፡ ህዝብ ፡ ሊያየኝ ፡ ሊሳለቅብኝ ለካ ፡ ተዐምራት ፡ በጣም ፡ የሚያምረው እግዚአብሔር ፡ ከሰማይ ፡ ሲያረፋፍድ ፡ ነዉ ባልጠፋ ፡ ሰዓት ፡ በሌሊት ፡ ተነስቶ ያገላብጥ ፡ ጀመር ፡ መዝገቤን ፡ ጐትቶ የፋርስና ፡ ሜዶን ፡ ህግ ፡ ተገልብጧል ሃማ ፡ መሞቻዉን ፡ አሳምሮ ፡ ሰርቷል የሚሞተውን ፡ ሰው ፡ አትሞትም ፡ ብሎታል የመኖሪያ ፡ ፈቃድ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰጥቶታል በእርሱ ፡ እድሜ ፡ አይቀለድም (፬x) በራዕዩ ፡ ምክንያት ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ቢጣልም እግዚአብሔር ፡ አላለም ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ አይቀርም መቼ ፡ ጓዳ ፡ ቀረ ፡ በጉድጓድ ፡ ተውጦ አደባባይ ፡ ወጥቷል ፡ ነገር ፡ ተገልብጦ በግብጽ ፡ በአካባቢው ፡ በአገር ፡ ሰው ፡ እያለ ተሸጦ ፡ የመጣው ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ቁጭ ፡ አለ ፈርኦን ፡ በቤቱ ፡ ቢኖርም ፡ ባይኖርም ጌታ ፡ ንጉሥ ፡ ካለህ ፡ መሾምህ ፡ አይቀርም አዝ:- እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ (፪x) እድለኛ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እድለኛ እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ለአምልኮ ፡ ማን ፡ ይቀድመኛል (፪x) እድለኛ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አዲስ ፡ እድሜ ፡ ከሰማይ ፡ የሰጠኛ ለአምልኮ ፡ ማን ፡ ይቀድመኛል