Loading
Singer
ደስ ፡ የሚልህን ፡ ስጦታ በእጄ ፡ ያለኝን ፡ ጌታ ራሴን ፡ ላድርግ ፡ መስዕዋትህ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ የምሰጥህ ኑሮህን ፡ ጨርሰህ ፡ በእኔ ፡ ኑር ካሰብከው ፡ የሚቀርህ ፡ አይኑር (፪x) በአንተ ፡ መኖር ፡ ያሰብከውን ፡ መኖር ኑሮህን ፡ መኖር ፡ መርጫለሁ ብኖር ፡ ለአንተ ብሞትም ፡ ለአንተ ከፈቃድህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ኑሮ/ሕይወት ፡ አይታየኝም ፡ እኔ (፪x) በላይ ፡ ያለው ፡ ፈቅድህ በምድር ፡ በእኔ ፡ እንዲሆን ይኸው ፡ ራሴን ፡ አምጥቻለሁ ለአንተ ፡ እንዲሆን ፡ ሰጥቻለሁ ለክብርህ ፡ መገለጫ ፡ ዕቃ የወደድከውን ፡ ማድረጊያ (፪x) እንደ ፡ ወትሮው ፡ በሥጋዬ ከብሮ ፡ ሳየው ፡ ውድ ፡ ጌታዬ ልጁን ፡ በእኔ ፡ መልክ ፡ ገልጦት ያሰበውም ፡ ሰምሮለት ደስታዬ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ ይሞላል መሻቴ ፡ ፍጻሜን ፡ ያገኛል (፪x) በአንተ ፡ መኖር ፡ ያሰብከው ፡ መኖር ኑሮህን ፡ መኖር ፡ መርጫለሁ ብኖር ፡ ለአንተ ብሞትም ፡ ለአንተ ከፈቃድህ ፡ ስር ፡ ይሁን ፡ መቃብሬ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ኑሮ/ሕይወት ፡ አይታየኝም ፡ እኔ (፪x)