Loading
Singer
አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x) እወጣለሁ ፡ እገባለሁ ፡ እሰማራለሁ የኢየሱስን ፡ ሰላም ፡ በሕይወቴ ፡ አያለሁ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ ምህረቱ ፡ ከቦኛል በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ሰላም ፡ ሆኖልኛል አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x) ማህበሉ ፡ ቢነሳም ፡ እንኳን ፡ ወጀቡም ፡ ቢበዛ ነፍሴ ፡ እረፍት ፡ አላት ፡ በኢየሱስ ፡ ተይዛ በለስ ፡ ፍሬ ፡ ባታፈራ ፡ የወይራ ፡ ስራም ፡ ቢጐል እኔ ፡ ግን ፡ በአምላኬ ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x) የልቤ ፡ ጥያቄ ፡ ሞልቶ ፡ ሁሉ ፡ ቢሆንልኝ ለእኔስ ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ አንድም ፡ አይሆንልኝ የተሰወረውን ፡ ነገር ፡ የውስጥን ፡ ይረዳል በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x) ከታሰርኩበትም ፡ ፈቶ ፡ ነጻ ፡ አድርጐኛል ውዴ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ከብሯል ፡ ከፍ ፡ ብላል ኃጢአቴን ፡ አስወግዶልኝ ፡ ፅድቄ ፡ እርሱ ፡ ሆናል በፊቱ ፡ ዘላለሁ ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለኛል አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፪x) ኢየሱስ ፡ መልካም ፡ እረኛ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ መልሷታል በፅድቅም ፡ መንገድ ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መርቷታል በጌታዬ ፡ በኢየሱስ ፡ በእርሱ ፡ እመካለሁ በእርሱ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ለእርሱ ፡ እገዛላሁ አዝ፦ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በኢየሱሴ/በአምላኬ ደስ ፡ ይለኛል ፡ በጌታዬ ሰላም ፡ ጤና ፡ ሆኗል ፡ ለኑሮዬ (፬x)