Loading
Singer
እያንዳንዱ ፡ ቀን ፡ ክፉ ፡ ነው መልካም ፡ መዓዛ ፡ ጣዕምም ፡ የለው የትም ፡ ብንሄድ ፡ ምንም ፡ ብንይዝ ሁሉም ፡ ነገር ፡ አለው ፡ መዘዝ ነገር ፡ ግን ፡ ዓይኖቻችንን ፡ ወደ ፡ ጌታ ፡ ስናቀና የሚያስደስተን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሚሞላን ፡ በምሥጋና እስቲ ፡ የላዩን ፡ እናስብ ፡ የምድሩን ፡ እንተወውና ደስ ፡ ይበለን (፬x) ሃሴት ፡ እናርግ ፡ ዕልል ፡ እንበል በምድር ፡ ጥበብ ፡ ጥበበኞች ሃያላን ፡ ባላባቶች ብርቱዎችም ፡ ደግሞ ፡ እያሉ የሰውን ፡ ምስፈርት ፡ የሚያሟሉ ሥጋን ፡ የለበሰ ፡ ሁሉ ፡ እንዳይመካ ፡ በከንቱ የዓለምን ፡ ሞኝ ፡ ምናምንቴ ፡ ደካማዎችን ፡ መምረጡ የሚያስፈነድቅ ፡ ተዓምር ፡ ነው ፡ እንደ ፡ እኛ ፡ ዓይነቱን ፡ መጥራቱ ደስ ፡ ይበለን (፬x) ሃሴት ፡ እናርግ ፡ ዕልል ፡ እንበል በልዩ ፡ ልዩ ፡ ፈተና ፡ ሃዘን ፡ ዛሬ ፡ ቢጐበኘንም እምነታችን ፡ እንዲነጥር ፡ ፈትና ፡ ቢደርስብንም ከተዘጋጀልንና ፡ ሊገለጥልን ፡ ካለው ፡ ክብር ልንወርሰው ፡ ከምንጥብቀው ፡ ከማይጠፋው ፡ ርስታችን ፡ ጋር ሲመዛዘን ፡ ሥፍራም ፡ የለው ፡ ከቶም ፡ አይገባም ፡ ከቁጥር እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ደስ ፡ ይበለን እኛም ፡ ደግሞ ፡ ሕዝቡ ፡ ደስ ፡ ይበለን በክርስቶስ ፡ ዋጅቶን ፡ ደስ ፡ ይበለን አርጐናል ፡ ገንዘቡ ፡ ደስ ፡ ይበለን ከሞት ፡ መንጋጋ ፡ ውስጥ ፡ ደስ ፡ ይበለን ነጥቆ ፡ አውጥቶናል ፡ ደስ ፡ ይበለን በክንዱ ፡ መድሃኒት ፡ ደስ ፡ ይበለን ሕያዋን ፡ አርጐናል ፡ ደስ ፡ ይበለን