Loading
Singer
እልፍ ፡ ጥያቄ ፡ እልፍም ፡ ችግር ታቅፎ ፡ የኖረ ፡ ሳያንገራግር ችግሩን ፡ ቻል ፡ አድርጎ ጌታ ፡ ይበልጣል ፡ ብሎ ሲያመልክ ፡ ባደባባይ ይሰማ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ይታይ አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ ድረስለት ፡ ለእንዲህ ፡ ዓይነቱ ፡ ሰው (፪x) ባዶውን ፡ እንዲሁ ፡ አትመልሰው (፪x) ሲማፀን ፡ በቆመበት ፡ ስፍራ (፪x) አለሁ ፡ በለው ፡ ስምህን ፡ ሲጠራ (፪x) አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ ከወገኖቹ ፡ ከሀገር ፡ እርቆ በባእድ ፡ ምድር ፡ ሚኖር ፡ ተሳቆ ያሰበው ፡ ባይሞላለት ፡ ሲያለቅስ ፡ በያለበት ራራ ፡ ስማው ፡ አቤቱ አለሁ ፡ በል ፡ ለእንዲህ ፡ ዓይነቱ አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ ድረስለት ፡ ለእንዲህ ፡ አይነቱ ፡ ሰው (፪x) ባዶውን ፡ እንዲሁ ፡ አትመልሰው (፪x) ሲማፀን ፡ በቆመበት ፡ ስፍራ (፪x) አለሁ ፡ በለው ፡ ስምህን ፡ ሲጠራ (፪x) አዝ፦ ይረዳል ፡ ይበል ፡ ተረድቶ ያግዛል ፡ ይበል ፡ ታግዞ