Loading
Singer
ኮረብታውን ፡ ወጥቼ ፡ እፎይ ፡ አልኩኝ ድንቅ ፡ የሆኑ ፡ ፍጥረታትን ፡ እያየሁኝ ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ለማለት ፡ አልደፈርኩም በዙሪያዬ ፡ አጫዋች ፡ አላጣሁም አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ ቀስ ፡ እያልኩኝ ፡ ቀጠልኩኝ ፡ እርምጃዬን አቤት ፡ ወፎች ፡ ከበውኛል ፡ ዙሪያዬን ልዩ ፡ ልዩ ፡ ቀለም ፡ ለብሰው ፡ ሲጫወቱ ደስ ፡ ያሰኛል ፡ የአምላክ ፡ ጥበብ ፡ መሰረቱ አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ ሽው ፡ እያለ ፡ በሚያዝናናኝ ፡ ነፋስ ፡ ደግሞ ሲወዛወዝ ፡ የ. (1) . ፡ አንገት ፡ ዘሞ አንዴ ፡ ቀና ፡ አንዴ ፡ ጐንበስ ፡ አቤት ፡ . (2) . እንዴት ፡ ሰራው ፡ ታላቅ ፡ ጌታስ ፡ ያሰኛል አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ የአበቦቹ ፡ መዓዛ ፡ እያወደኝ ልዩ ፡ ቃና ፡ ለአካላቴ ፡ እየሰጠኝ በአምላክ ፡ እጆች ፡ በተሰሩት ፡ ተደንቄ ተመለስኩኝ ፡ ወደ ፡ ቤቴ ፡ ብዙ ፡ አውቄ አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ