Loading
Singer
አዝ፦ ድንቅ ፡ ነው ፡ ያረገልኝ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ድንቅ ፡ ነው ፡ የሰራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ምን ፡ ብዬ ፡ ልናገረው ምን ፡ በዬ ፡ ልመልሰው ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ምን ፡ ብዬ ፡ ልናገረው ምን ፡ በዬ ፡ ልመልሰው ውለታው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x) አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ክብር አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ አለኝ ፡ ክብር ይክበር ፡ እግዚአብሔር (፪x) በለቅሶ ፡ ዘርን ፡ የዘራሁት (አሃ) አምላኬ ፡ ባየልኝ ፡ ብዬ ፡ ያልኩትን (አሃ) የሃዘን ፡ ማቄን ፡ አወለቀና (አሃ) ሳቅ ፡ ሆነ ፡ ቤቴ ፡ ጌታ ፡ ገባና ፡ አሃ ፡ ጌታ ፡ ገባና (፪x) ያደረገው (አሃ)፡ እጅግ ፡ ብዙ (አሃ) ለውለታው (አሃ) ፡ ምሥጋና ፡ አብዙ (አሃ) የሰራልኝ (አሃ) ፡ እጅግ ፡ ብዙ (አሃ) ለውለታው (አሃ) ፡ ምሥጋና ፡ አብዙ (አሃ) እንዲህ ፡ በሉ (አሃ) ፡ አመስግኑ (አሃ) ዕልል ፡ በሉ (አሃ) (፪x) የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ የምሥጋና ፡ የዝማሬ (፬x) አዝ፦ ድንቅ ፡ ነው ፡ ያረገልኝ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ድንቅ ፡ ነው ፡ የሰራልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ምን ፡ ብዬ ፡ ልናገረው ምን ፡ በዬ ፡ ልመልሰው ውለታው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ምን ፡ ብዬ ፡ ልናገረው ምን ፡ በዬ ፡ ልመልሰው ውለታው ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው አለኝ ፡ ምሥጋና ፡ አለኝ ፡ ክብር አለኝ ፡ ዕልልታ ፡ አለኝ ፡ ክብር ይክበር ፡ እግዚአብሔር (፪x) ለምስኪኑ ፡ ሰው ፡ ምንጭ ፡ አፍልቀሃል ለደካከመው ፡ ሞገስ ፡ ሆነሃል ምድረ ፡ በዳውን ፡ ያለመለምከው በቅኔ ፡ መዝሙር ፡ ስምህን ፡ ያክብረው አሃ ፡ ስምህን ፡ ያክብረው (፪x) የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ የምሥጋና ፡ የዝማሬ (፬x) ያደረገው (አሃ)፡ እጅግ ፡ ብዙ (አሃ) ለውለታው (አሃ) ፡ ምሥጋና ፡ አብዙ (አሃ) የሰራልኝ (አሃ) ፡ እጅግ ፡ ብዙ (አሃ) ለውለታው (አሃ) ፡ ምሥጋና ፡ አብዙ (አሃ) እንዲህ ፡ በሉ (አሃ) ፡ አመስግኑ (አሃ) ዕልል ፡ በሉ (አሃ) (፪x)