Loading
Singer
በበደል ፡ በሀጥያት ፡ ሙታን ፡ የነበርነው ከመንግስቱ ፡ ጠፍተን ፡ ተጨንቀን ፡ ላለነው ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ህይወትን ፡ አገኘን በርግጥ ፡ ሞተን ፡ ነበር ፡ በፀጋው ፡ አዳነን (፪x) አዝ፡ ፡ ድነናል ፡ ድነናል ፡ በፀጋው ፡ ድነናል ፡ /3 በጠላት ፡ እስራት ፡ በጨለማ ፡ ሆነን መሄጃው ፡ ጠፍቶብን ፡ ተስፋ ፡ ቆርጠን ፡ ሳለን አርነት ፡ ሊያወጣን ፡ ስለኛ ፡ ቆሰለ ሞታችንን ፡ ሞቶ ፡ በህይወት ፡ አኖረን (፪x) አዝ፡ ፡ ድነናል ፡ ድነናል ፡ በፀጋው ፡ ድነናል ፡ /3 በርግጥ ፡ ሞተን ፡ ነበር ፡ በጌታ ፡ ድነናል የዘላለም ፡ ህይወት ፡ በነፃ ፡ አግኝተናል ክሳችንን ፡ ከኛ ፡ ከኛ ፡ ላይ ፡ ወስዶታል ማይጠፋውን ፡ ህይወት ፡ በነፃ ፡ አግኝተናል (፪x)