Loading
Singer
ስሬት ፡ ያለበት ፡ ፈውስ አሮጌነትን ፡ ሽሮ ፡ የሚያደርግ ፡ አዲስ በደልን ፡ ሊያስወግድ ፡ ፈፅሞ ፡ ኃይል ፡ ያለው የጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ያ ፡ ክብሩ ፡ ደሙ ፡ ነው አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፪x) በደም ፡ የጠበቀ ፡ ቃልኪዳን ፡ ላይሻር ሊፋቅ ፡ ሊደመሰስ ፡ ከቶ ፡ እንዳይሞከር ስለገባው ፡ ጠላት ፡ በደም ፡ ተማምሎ ሊገድለኝ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ጥርሶቹን ፡ አሹሎ ወደ ፡ እኔ ፡ ሲመጣ ፡ በእራሱ ፡ ተማምሎ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በእኔ ፡ ቦታ ፡ ሆኖ ያ ፡ የደምን ፡ ቃልኪዳን ፡ በደሙ ፡ አምክሮ ሕይወት ፡ ሆነልኝ ፡ ነውሬን ፡ ሸፍኖ አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፪x) በሰሩት ፡ ኃጢያት ፡ ልክ ፡ ማሰሪያ ፡ እንዲሆን ይሰዉ ፡ ነበረ ፡ የእንስሳቶችን ፡ ደም አቅም ፡ ያለውማ ፡ ይሰረይለታል መስዕዋት ፡ የሌለው ፡ እያነባ ፡ ይኖራል አለ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት የሚራራ ፡ ሁሌ ፡ ለልጆቹ ፡ ሕይወት መቅረብ ፡ እንዲችሉ ፡ ፊቱ ፡ በእኩልነት ታሪክ ፡ ቀያየረ ፡ እርሱ ፡ ሆነ ፡ መስዕዋት አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፪x) አስጠንቅቆት ፡ ነበር ፡ የሞትን ፡ መልዓክ የእስራኤልን ፡ ሰፈር ፡ ከቶ ፡ እንዳይታወክ የተነገረውም ፡ እንደዚህ ፡ እኮ ፡ ነው ደንበር ፡ ላይ ፡ ካለ ፡ ትቶ ፡ እንዲያልፍ ፡ ነው አዎ ፡ በእኔ ፡ መንደር ፡ መታወክ ፡ አይሆንም አሳልፎ ፡ አይሰጠኝ ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም ዛሬም ፡ ተማምኜ ፡ ኮራ ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ በደም ፡ ነው ፡ የገዛኝ ፡ ዋጋዬ ፡ ውድ ፡ ነው አዝ፦ ደሙ ፡ ኃይል ፡ ጉልበቴ ደሙ ፡ ሥር ፡ መሠረቴ ደሙ ፡ ሆነኝ ፡ ብቃቴ ደሙ ፡ መድኃኒቴ (፬x)