Loading
Singer
ደሙ (፲፪x) የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል አሜን ፡ ያነፃል ፡ ያጸድቃል በመላለሻ ፡ በአደባባይ እርቃኑን ፡ ተሰቅሎ ፡ ለሰው ፡ ልጅ ፡ ሲታይ በግፍ ፡ እየተገፋ ፡ ተራራን ፡ ነጎደ በቀራኒዮ ፡ ስፍራ ፡ በመስቀል ፡ ሞተ አይተው ፡ እንዳይወዱ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ የለውም እጅግ ፡ የተጠላ ፡ ቁስለኛ ፡ ነው ታዲያ ፡ ይሄማ ፡ እንዴት ፡ መድሀኒት ፡ ይሆናል ያለው ፡ ሁሉ ፡ ይስማ ፡ ደሙ ፡ ያነፃል የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል አሜን ፡ ያነፃል ፡ ያጸድቃል እንደ ፡ አሮን ፡ ልጆች ፡ ክህነት ፡ እንደሌዊ ፡ ዘር ፡ ስርዐት አይደለም ፡ የውዴ ፡ አይደለም ፡ የውዴ የኮርማ ፡ እና ፡ የዋኖስን ፡ ደም መች ፡ ይዞ ፡ ገባ ፡ እኔን ፡ ለማፅደቅ ሥጋውን ፡ አንዴ ፡ አቅርቦ ፡ ዘላለም ፡ ያማረ ደሙ ፡ ፈሰሰና ፡ ኃጥያቴ ፡ ተሻረ በቀራኒዮ ፡ ሞቱ ፡ ዳግም ፡ ወለደና አብን ፡ አባ ፡ አልኩት ፡ ልጅ ፡ ነሽ ፡ ተባልኩና የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል የክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከኃጥያት ፡ ሁሉ ፡ ያነፃል የልጁ ፡ የኢየሱስ ፡ ደም ፡ ከበደል ፡ ሁሉ ፡ ያጸድቃል አሜን ፡ ያነፃል ፡ ያጸድቃል