Loading
Singer
የሕይወቴንም ፡ ምእራፍ ፡ አቅጣጫ ፡ የለወጠ ድንጋይ ፡ ልብ ፡ ወስዶ ፡ ስጋ ፡ ልብ ፡ የሰጠ ድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ሕይወቴን ፡ ያበራ የእርሱን ፡ ውለታ ፡ ዳግም ፡ ዳግም ፡ ላውራ አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብር ፡ አወራለሁ ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል የመከራ ፡ ውሃ ፡ እየተጐነጨ ላቡን ፡ በከንቱ ፡ ለበረሃ ፡ የረጨ ዛሬ ፡ ታድሶ ፡ ወዙ ፡ ተመልሷል መቅደሱ ፡ ገብቶ ፡ አምላኩን ፡ ያነግሳል አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብር ፡ አወራለሁ ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል ጉልምስናዬ ፡ ወንጌል ፡ አገልግሎ ሕይወቴ ፡ አላማው ፡ በአንተ ፡ ተጠቃሎ አንተን ፡ አንግሼ ፡ አንተን ፡ የማይበት ይሁን ፡ ሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ንገሥበት አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብሩን ፡ አወራለሁ ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል ዛሬም ፡ ጌታዬ ፡ ነፃነት ፡ ይሰጣል ከዙፋኑ ፡ ፊት ፡ በረከት ፡ ይወጣል ስሙን ፡ ላነግሥ ፡ በፊቱ ፡ ቆሜያለሁ ሕይወቴን ፡ በድል ፡ እፈጽማታለሁ አዝ:- ኮረብታ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ድሉን ፡ አውጃለሁ የመንግስቱን ፡ ግርማ ፡ ክብሩን ፡ አወራለሁ ዛሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ዛሬም ፡ ያክንዱ ፡ ይሰራል የድል ፡ ወንጌል ፡ ይሄው ፡ በአለም ፡ ይነገራል (፪x)