Loading
Singer
የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የማመልከው (፫x) አታልቅስ ፡ ብሎ ፡ ከሃዘኔ ፡ ያጽናናኝ ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ ያበረታኝ (፪x) መጽሃፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ ገናናው/ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x) ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አዎ ቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x) ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አሜን ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x) መለከት ፡ ይነፋ ፡ ይወራለት ፡ ዝናው አዋጁም ፡ ይታወጅ ፡ እንዳይኖር ፡ ያልሰማ ሞት ፡ መውጊያው ፡ ተሰብሮ ፡ ጉልበቱ ፡ ደቀቀ ሲኦል ፡ ተሸነፈ ፡ ቁልፉ ፡ ተነጠቀ ይህን ፡ ማድረግ ፡ የቻለ ፡ ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ማነው አያንስበትም ፡ ወይ ፡ ታድያ ፡ ከዚህ ፡ በላይ ፡ ባመልከው ይህን ፡ ላደረገው ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው ይህን ፡ ላደረገው ፡ ስለሚገባው አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት ይድመቅ ፡ ዕልልታው ፡ ስለሚገባው (፬x) የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ የማመልከው (፫x) አታልቅስ ፡ ብሎ ፡ ከሃዘኔ ፡ ያጽናናኝ ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ ያበረታኝ (፪x) መጽሃፉን ፡ ወስዶ ፡ ማኅተሙን ፡ የፈታ የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ የጌቶቹ ፡ ጌታ ከይሁዳ ፡ ነገድ ፡ የሆነው ፡ አንበሳ ገናናው/ኃይለኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x) ብቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አዎ ቻውን ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x) ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ ፡ አሜን ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ (፪x) ጌታዎች ፡ ባርያዎች ፡ ድሆች ፡ ባለጸጋዎች ታናናሽ ፡ ታላላቅ ፡ ሃያላን ፡ ደካሞች ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ የሚምበረከክለት ሕያውም ፡ ግዑዙም ፡ የሚንቀጠቀጥለት እረ ፡ እንዴት ፡ ምስጉን ፡ ነው ፡ ወዶ ፡ የሚያመልከው በዕልልታ ፡ በሆታ ፡ ስሙን ፡ ያወደሰው ይህን ፡ ላደረገው ፡ አምልኮ ፡ ይብዛለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት ይህን ፡ ላደረገው ፡ ይድመቅ ፡ ዕልልታው ይህን ፡ ላደረገው ፡ ስለሚገባው አምልኮ ፡ ይብዛለት ፡ ክብር ፡ ይጨመርለት ይድመቅ ፡ ዕልልታው ፡ ስለሚገባው (፬x)