Loading
Singer
አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ግብረ ፡ ጉንዳን ፡ መኖዋን ፡ በበጋ ፡ አሰናድታ ክረምት ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ ትበላለች ፡ ተኝታ ጻድቅ ፡ በምቹ ፡ ጊዜ ፡ በአንተ ፡ ፊት ፡ ከተጋ ዋስትና ፡ አለውና ፡ ይኖራል ፡ ምንም ፡ ሳይሰጋ አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ካልተጠበቀ ፡ መንጋ ፡ ማነው ፡ ወተት ፡ የሚሻ? ያልዘሩትን ፡ ለማጨድ ፡ አይኬድም ፡ ወደ ፡ እርሻ ጥያቄ ፡ በመጣ ፡ ጊዜ ፡ እምነቴ ፡ እንዳይከዳኝ ዛሬ ፡ ቀን ፡ ሳለ ፡ ጌታ ፡ ፍቃድህን ፡ ልፈጽም ፡ እርዳኝ አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ትጥቄን ፡ ሳላጠባብቅ ፡ እንዲያው ፡ መሮጥ ፡ ካሰኘኝ ተጠልፌ ፡ ወድቄ ፡ ጠላት ፡ እንዳያገኘኝ ዛሬ ፡ ስራኝ ፡ በጓዳ ፡ በአደባባይም ፡ አይደል ኋላ ፡ አያቅተኝም ፡ በአንድ ፡ ጠጠር ፡ ሺህ ፡ መግደል አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ከተከፈተ ፡ ሰማይ ፡ ወርቃማ ፡ ቅባት ፡ ፈሶ ጸጋህ ፡ በውስጤ ፡ ይሙላ ፡ መንፈሴን ፡ አረስርሶ ደዌን ፡ እገስጻለሁ ፡ መናፍስትን ፡ አዛለሁ ጭፍሮችን ፡ አባርሬ ፡ ምርኮን ፡ እበዘብዛለሁ አዝ፦ አቤቱ ፡ ድካሜን ፡ አንሳ ፡ ከላዬ ኃይልን ፡ አልብሰኝ ፡ ጌታዬ (፪x)