Loading
Singer
አንዴ ፡ ድኛለሁ ፡ ጽድቅን ፡ ጸድቄ በከበረው ፡ ደም ፡ ከአብ ፡ ታርቄ የቃልኪዳን ፡ ልጁ ፡ አድርጐኛል ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ ማን ፡ ይለየኛል (፪x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ በአንዱ ፡ አዳም ፡ ምክንያት ፡ ሞት ፡ ወደእኛ ፡ መጣ አልታዘዝ ፡ ብሎ ፡ ከገነት ፡ ሊወጣ አምላክ ፡ ሥጋ ፡ ለብሶ ፡ ወደምድር ፡ ወረደ ራሱን ፡ ቤዛ ፡ አድርጐ ፡ ሊያጸድቀን ፡ ወደደ አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ እግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ ሎሌ ፡ ሳልሆን ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ ዘምሬ ፡ አልጠግብም ፡ ስለመዳኔ ሌላው ፡ ሌላውማ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ አንዴ ፡ ድኛለሁ ፡ ጽድቅን ፡ ጸድቄ በከበረው ፡ ደም ፡ ከአብ ፡ ታርቄ የቃልኪዳን ፡ ልጁ ፡ አድርጐኛል ከእርሱ ፡ ፍቅር ፡ ማን ፡ ይለየኛል (፪x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ በማመኔ ፡ ብቻ ፡ ሳልደክም ፡ ሳልለፋ ዘለዓለሜ ፡ አማረልኝ ፡ አምላክ ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ እውነትም ፡ መንገድም ፡ ሕይወትም ፡ እርሱ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ ብዬ ፡ እመሰክራለሁ አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ እግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ አቤት ፡ አቤት ፡ እገረማለሁ ፡ እደነቃለሁ ሎሌ ፡ ሳልሆን ፡ ልጅ ፡ በመሆኔ ፡ እደሰታለሁ ዘምሬ ፡ አልጠግብም ፡ ስለመዳኔ ሌላው ፡ ሌላውማ ፡ ትርፍ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ ፡ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ፡ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ፡ ሆኛለሁ ፡ አሮጌው ፡ አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ ፡ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ ፡ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ፡ ነህ ፡ አለኝ ፡ የስሜ ፡ ዜጋ