Loading
Singer
እንዲህ ፡ ያለ ፡ መውደድ ፡ ከቃላት ፡ ያለፈ ስለጠላቶቹ ፡ ነፍሱን ፡ ያሳለፈ ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ተደንቆ ፡ ዋለ ፍቅር ፡ እንዳንተ ፡ የለም ፡ እያለ ፀሐይም ፡ አለች ፡ ብርሃን ፡ ለምኔ መስቀል ፡ ላይ ፡ ሲውል ፡ ደጉ ፡ መድህኔ አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ ወደ ፡ ሙት ፡ ሲነዳ (ደግ ፡ ነህ) የአዳም ፡ ዘር ፡ በሙሉ (ደግ ፡ ነህ) ሞቱን ፡ ሞተህለት (ደግ ፡ ነህ) ደርሰህ ፡ ካለህ ፡ ሁሉ (ደግ ፡ ነህ) ነፍስን ፡ እስከመስጠት (ደግ ፡ ነህ) ፍቅርህ ፡ ተፈትኖ (ደግ ፡ ነህ) ከፍርድ ፡ አመለጠ (ደግ ፡ ነህ) ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ሆኖ (ደግ ፡ ነህ) አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ ለፃድቅ ፡ የሚሞት ፡ በጭንቅ ፡ ከተገኘ አጥቶ ፡ ተስፋ ፡ ቆርጦ ፡ መኖር ፡ ባልተመኘ ግን ፡ ተገለጠ ፡ ፍቅር ፡ ለሁሉ አመለጡብህ ፡ ጌታን ፡ እያሉ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ያንተስ ፡ ፍቅር መሰከሩልህ ፡ ሰማይ ፡ ምድር ፡ አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ አቅም ፡ አጥተህ ፡ አይደል ፡ ተሸንፈህ በጨካኞች ፡ ጡንቻ ፡ ላይ ፡ መውደቅህ እንደሚታረድ ፡ በግ ፡ እየነዱ በመስቀል ፡ ሊገሉህ ፡ ወደዱ (፪x) አዝ፦ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢደንቃቸው ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አሉህ ባህሪህ ፡ ባህሪህ ፡ ቢያስገርመኝ ፡ ደግ ፡ ነህ ፡ አልኩህ አወይ ፡ አጨካከን ፡ ጠፍቶ ፡ የሚራራ እያወካከቡ ፡ ነዱት ፡ በተራራ አፉ ፡ አልተከፈተ ፡ ክፉ ፡ አልተናገረ ጭራሽ ፡ ለሚጠሉት ፡ ይማልድ ፡ ጀመረ ወዶ ፡ አለም ፡ ቢያወድሰው በእርግጥ ፡ ስለሚገባው ፡ ነው ለእኛ ፡ ብሎ ፡ ታርዷል ፡ እና ለእርሱ ፡ ይገባል ፡ ምስጋና (፪x)