Loading
Singer
ኢየሱስን ፡ አምኖ ፡ የሕይወቱ ፡ ጌታ ፡ ንጉሱ ፡ ያረገ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ጌታን ፡ በማመኑ ፡ እንደ ፡ ሃይማኖት ፡ ከጂ ፡ አርጐ ፡ የተቆጠረ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) ቀድሞ ፡ ከነበሩት ፡ ከባልንጀሮቹ ፡ ተለይቶ ፡ ሄደ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ላመነበት ፡ ነገር ፡ አንገቱን ፡ ለካራ ፡ ሊሰጥ ፡ የጨከነ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x) በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤይ) ሌሎች ፡ እንዲድኑ ፡ የምስራቹን ፡ ቃል ፡ ይዞ ፡ የተጓዘ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) በተሰጠው ፡ መክሊት ፡ ፀጋ ፡ እየሰራ ፡ ብዙ ፡ ያተረፈ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) በስሜቱ ፡ ሳይሆን ፡ በእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ውሳኔ ፡ ወሰነ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) በዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ለሚገኘው ፡ አክሊል ፡ ሲልም ፡ ተሯሯጠ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x) በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ) ብዙ ፡ ምርጫ ፡ እያለው ፡ አምላኬ ፡ መረጠው ፡ ይሻለኛል ፡ ያለ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ደስታው ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ እንጂ ፡ በዚች ፡ ዓለም ፡ ፈጽሞ ፡ ያልሆነ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) ቃል ፡ እየተሞላ ፡ በከበበው ፡ ችግር ፡ ላይ ፡ እየመዘዘ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ድል ፡ በድል ፡ የሚሄድ ፡ ድካሙን ፡ አራግፎ ፡ ቆርጦ ፡ የተጓዘ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x) በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ) ሰው ፡ ሲያስቀይመው ፡ ምህረትና ፡ ይቅርታ ፡ ለሁሉ ፡ ያረገ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) በቀል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ሁሉን ፡ ትቶ ፡ ለፍቅር ፡ የኖረ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) ህሊናው ፡ የጸዳ ፡ በሰዎች ፡ ጉዳይ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ፡ ያልፈተፈተ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ሁሉን ፡ ሰው ፡ የሚያውቀው ፡ በክርስቶስ ፡ ብቻ ፡ በሌላ ፡ ያልሆነ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x) በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ) ምሥጋና ፡ ለመስጠት ፡ መስዕዋት ፡ ለማቅረብ ፡ ወደኋላ ፡ ያላለ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ከማንም ፡ ከምንም ፡ አምላኩን ፡ ለማክበር ፡ እራሱን ፡ የሰጠ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) ውለታ ፡ የማይረሳ ፡ ድንቅ ፡ ተዓምራቱን ፡ ለሁሉ ፡ የነገረ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤኤ ፤ ደግ ፡ አረገ) ሁልጊዜ ፡ ምሥጋና ፡ ከአፉ ፡ የማይጠፋ ፡ ዕልልታን ፡ ያወቀ (ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ ፤ ደግ ፡ አረገ) አዝ፦ ደግ ፡ አረገ ፡ ማለት ፡ ደጐ ፡ ለሚታየው መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (፪x) በቃላቱ ፡ ሳይሆን ፡ ፊደሉን ፡ ካየነው መልካም ፡ ላረገ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ላረገ ፡ ነው ለአንዱ ፡ ማብሸቂያ ፡ ነው ለሌላው ፡ እንኳን ፡ ነው ለእኔ ፡ ደግ ፡ አረገ መልካም ፡ ንግግር ፡ ነው (ደግ ፡ አረገ ፡ ነው ፤ ደግ ፡ አረገ ፡ ኤሂ)