Loading
Singer
አብን ፡ በዙፋኑ ፡ ወልድን ፡ በስተቀኙ በምድር ፡ የተገፋውን ፡ በክብር ፡ ሊገናኙ ሲጋብዙት ፡ ታይቶት ፡ ክርስቲያን ፡ በጣሩ ተፈፀመ ፡ ብሎ ፡ ወጣ ፡ ከሃሩሩ አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ እውር ፡ ፈሪሳውያን ፡ በምናቸው ፡ ይዩ ፀዳል ፡ መፈንጠቁን ፡ ከችግር ፡ ትይዩ በመከራ ፡ ናዳ ፡ በሰዎች ፡ ጫጫታ ሩጫውን ፡ አከተመ ፡ ጀግናው ፡ ሳይረታ አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ ሃገር ፡ ሃገር ፡ ሲዞር ፡ ሲንከራተት ፡ ከርሞ መልኩ ፡ ተቀይሮ ፡ በመከራ ፡ ከስሞ ከጅራፍ ፡ ከዱላ ፡ ከጨካኞች ፡ ጡጫ ክርስቲያን ፡ አንቀላፋ ፡ አረፈ ፡ ከእርግጫ አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ እንደነ ፡ ያዕቆብ ፡ በደም ፡ ተበክለዉ ለወንጌል ፡ ሊደፉ ፡ ለቃልኪዳናቸው በሰልፍ ፡ ቆመዋል ፡ ተራ ፡ ይጠብቃሉ ኢየሱስ (፫x) ፡ ይላሉ አዝ፦ ለረጅም ፡ ዘመናት ፡ ተቸግሮ ፡ ማቆ ክርስቲያን ፡ ተሻገረ ፡ ወላፈኑን ፡ ዘልቆ