Loading
Singer
አዝ፦ ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ የለው ፡ ወደር ክብር ፡ ይሁንለት ፡ በሰማይ ፡ በምድር እልል ፡ በሉ ፡ ዘምሩለት ፡ በበገና አምልኮ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይገባዋልና ይገባዋል (፰x) ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃሉ ፡ ያጸና ሁሉን ፡ የፈጠረ ፡ ኃያል ፡ ባለዝና በእውነት ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ ፍፁም ፡ የታመነ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ኤልሻዳይ ፡ የሆነ ዘለዓለማዊ ፡ አምላክ ፡ ሁሉ ፡ ይቻለዋል አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ክብር ፡ ይገባዋል ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x) አዝ፦ ቸር ፡ ነውና ፡ ምህረቱ ፡ የለው ፡ ወደር ክብር ፡ ይሁንለት ፡ በሰማይ ፡ በምድር እልል ፡ በሉ ፡ ዘምሩለት ፡ በበገና አምልኮ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይገባዋልና ይገባዋል (፰x) የሞት ፡ አዋጅ ፡ ሽሮ ፡ ሕይወትን ፡ የሚሰጥ መራራውን ፡ ሃዘን ፡ በሳቅ ፡ የሚለውጥ አጥፊውን ፡ አጥፍቶ ፡ ምስኪኑን ፡ ያከብራል ሃሳቡ ፡ እንደዋዛ ፡ መቼ ፡ ይከለከላል ማደሪያው ፡ ይባረክ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት የፍጥረታት ፡ ጌታ ፡ የሕያዋን ፡ አባት ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)