Loading
Singer
አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x) ምነው ፡ መጨነቄ ፡ ረዳት ፡ እንደሌለው አሕዛብ ፡ ያውቃሉ ፡ በአንተ ፡ እቅፍ ፡ እንዳለሁ አጥፍቼም ፡ እንደሆን ፡ ቅጣኝ ፡ እንደ ፡ ልጅህ የለፋህብኝ ፡ ነኝ ፡ ፈሶልኛል ፡ ደምህ (፪x) አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x) በዓይን ፡ የማይታዩ ፡ ሠራዊቶች ፡ አሉኝ ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ሥር ፡ የሚያንጋልሉልኝ ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ለዓለም ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ አሁን ፡ ብንቀጠቀጥ ፡ ታድያ ፡ ምን ፡ ይላሉ (፪x) አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x) ጉድለቱን ፡ አውቃለሁ ፡ እኔው ፡ ነኝ ፡ ምክንያቱ ለስጋም ፡ ለነፍሴም ፡ እሾህ ፡ የሆንኩቱ አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ምህረት ፡ የተሞላህ ጠግነኝ ፡ በቁጣህ ፡ አስተምረኝ ፡ እንዳሻህ አዝ፦ ማለዳ ፡ ስነሳ ፡ ጭንቀተን ፡ ላዋይህ ነፍሴን ፡ ያዛላትን ፡ ችግሬን ፡ ላሳይህ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ፡ ምስጥረኛም ፡ የለኝ ኢየሱስ ፡ ፈጥነህ ፡ ናና ፡ ከሀዘኔ ፡ ገላግልኝ (፪x)