Loading
አንተ የሌለህበት ቦታ ለምኔ ሃገር ለምኔ ከፍታ ለምኔ አንተ የሌለህበት ህብረት ለምኔ መዝሙር ለምኔ ወሬ ለምኔ አስጠጋኝ ወደ እቅጅህ ወዳየህልኝ ወደ ሃሳብህ የእግሮቼን ጉዞ መትርልኝ የአንደበቴን ቃል ስፈርልኝ ለፈቃዴ ገደብን አብጅለት ሞገደኛው ልቤ ይወቅ ለከት አስተምረኝ በየት ልውጣ ማለት አስተምረኝ ምን ትላለ ማለት አይኖቼ እያዩ ቅጥቅጧን ሸንበቆ ደግፈህ ስታቆማኝ እያወቀ ልቤ የምጤሰውን ጧፍ ቀርበህ ስታበራኝ ጆሮዬ እየሰማ ለራስ ማልበቃውን ስታተርፈኝ ለሃገር በቀረልኝ እድሜ ከአንተ ሌላ ውጭ አፌ ምን የናገር አሁንም ብዛልኝ እንዲረዝም እድሜዬ አብልጬ ልጠጋህ እንድደምቅ ማታዬ ሁነኝ መዋያዬ በቀረልኝ ዘመን መንገዴ እየነጋ እስክሆን ሙሉ ቀን ዉሎ ካንተ ጋር አድሮና ሰንብቶ ማን በትናንት ቀረ ከአንተ ብዙ ቀድቶ የለውጥ ጅማሬ ነህ የሕይወት ማጣፈጫ የተጠጉህ ሁሉ ወጥተዋል በብልጫ ሰሞነኛ እንዳልሆን አድሮ እንዳልሰለች ጉልበቴን ላስጠጋ ወደ ቃሎችህ ደጅ ዘመንን ዘላቅ እንድሆን ነገሬ ዙረቴን አቁሜ ልፈልግህ ዛሬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.