Loading
አላረክም ብዬ አላማርርህም ደግሞ በሁኔታ ምስጋና አላቆምም ዘምርልሃለሁ ሁሌ ጥዋት ማታ እቀኝልሃለሁ የህይወት ጌታ ቢሞላ ደግሞ ባይሞላ ቢሣካ ደግሞ ማይሣካ ኧረ እኔ አላቆምም ምስጋና/2 ደመና ቢታይ ባይታይ ሽለቆ ቢሞላ ባይሞላ ኧረ እኔ አላቆምም እልልታ/2 ለምሥጋናዬ ምክንያት የሱስን ማወድስበት የተደረገልኝ በቂነዉ አግኝቻለሁ ህይወት ስለዚህ ሁልግዜ አላቆም መዘመር ያልተደረገልኝ አይዘኝም እኔን ቢሞላ ደግሞ ባይሞላ መንፈሳዊ ቅኔ ዝማሬ አምልኮዬን ጌታዬ በፊትህ ላቅርበዉ መስዋእቴን መንፈሴ እኮ ነቅትዋል በአንተ ትንሳኤ የማትቀየር ነህ ሁሌ ምስጋናዬ ምስጋናን ዝማሬን አለቆምም እልልታን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.